ካልቪናዊያን የሰከኑ እና ቸሮች ሊሆኑ ይገባል
ለአንድ ካልቪናዊ ቁጡ እና ደግነት የጎደለው ተደርጎ ከመግለጽ የከፋ መግለጫ እምብዛም የለም። እንዴት ነው የእግዚአብሔርን ትልቅነት ለመረዳት እየተፋለሙ ያሉ ሰዎች፣ መልሰው በመከራ ውስጥ ያለውን ኅብረተሰብ ሰላም የሚነሱት? ደግሞስ እንዴት ነው…
ለአንድ ካልቪናዊ ቁጡ እና ደግነት የጎደለው ተደርጎ ከመግለጽ የከፋ መግለጫ እምብዛም የለም። እንዴት ነው የእግዚአብሔርን ትልቅነት ለመረዳት እየተፋለሙ ያሉ ሰዎች፣ መልሰው በመከራ ውስጥ ያለውን ኅብረተሰብ ሰላም የሚነሱት? ደግሞስ እንዴት ነው…
አዶኒራም ጀድሰን (1788-1850) አዶኒራም ጀድሰን በሕይወት ዘመኑ የደረሱበት መከራዎች ታሪክ እጅግ አስገራሚ ነው። “ይህኛውስ አሰቃቂ ነው፤ ከዚህ የባሰ ምንም ሊደርስበት እና ሊቋቋመው አይችልም” ስትሉ ሌላ ደግሞ ይገጥመዋል። እንዲያውም ከእግዚአብሔር ረጅም…
ስለ ኀጢአቴ የእግዚአብሔርን ቁጣ ሰግቼ ከማለቅስበት ቀናት ይልቅ፣ የእግዚአብሔር መልካምነት ፍንጥቅታ ነክቶኝ ከልቤ የማለቅስበት ቀናት ይበዛሉ። አንድ ወቅት ባለቤቴን በቁጣ ከተናገርኩ በኋላ ከማዕድ ቤት ወጥቼ የተሰበሰበውን ቆሻሻ ወደ ውጪ ለማውጣት…
የእግዚአብሔርን የአሠራር መንገዶች ለማወቅ ያለንን ቸልተኝነትን በመቃረን፣ እርሱን ለማድነቅና ለማምለክ የእግዚአብሔርን መንገድ እንደ መሠረት በመጠቀም የሚናገሩ የተለያዩ ጽሑፎችን አንብቤአለሁ። እንዲሁም የተለያዩ ሰባኪዎች በየምስባካቸው በዚህ መንገድ ሲሰብኩ ሰምቻለሁ። ይህንንም ለማድረግ የሚጠቀሙት ቃል “ምስጢር ” የሚለውን አዎንታዊ ቃል ሲሆን በዚህም የእግዚአብሔርን ክቡርነትና ልዕልና ምን ያህል እንደማናውቅ ተረድተን መደነቅ እንዳለብን ይነግሩናል።
በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ የሚመሩ ደግሞ በቃል ከመቀበል ባለፈ በውስጣቸው አስተውሎትና እርግጠኝነት አላቸው። አንተ ግን ቆም ብለህ እንዴት እንደሆነ ጠይቀህ ታውቃለህ? ደሙ እንደ ምትሃት ነው የሚሠራው? በርግጥ በደሙ ውስጥ ኃይል ካለ፤ ይህንን እውነት እንዴት ነው መረዳት የሚቻለው? "ድንቅ ሥራን የሚሠራ ኃይል" በማለት ስናበሥር የሚገለጠው እውነት ምን ይሆን?
ይህ ጥያቄ በማገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን መሪዎች እና ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ብዙ ጊዜ የምሰማው ጥያቄ ነው። እና ለእነርሱ (ለአንባቢም) ከጽሑፉ በቀጥታ ወደ ነጥቡ፣ ወይም በተሻለ ሁኔታ ወደ ተግባራዊ ተዛምዶው የሚወስዳቸውን አስማታዊ ቀመር እንዳለኝ ከመናገር የበለጠ ደስታ የለኝም።
መለወጥ የቅዱሳት መጻሕፍት ዋና ሐተታ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በርግጥ ለጠቅላላው የመቤዠት ታሪክ መሠረት ነው። በተለይም መቤዠት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ባለው ተዛምዶ ከመለወጥ ጋር ይያያዛል። ከመለወጥ ውጪ እግዚአብሔርን በማዳኑ መንገድ ማወቅ አንችልም። የኃጢአትን ይቅርታ ማግኘት አንችልም። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እና የማዳኑ መንግሥት መግባት አንችልም።
ባለፉት ዓመታት በዓለም ውስጥ ባሉ ትልልቅ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበከው መልእክት ተቀይሯል። በርግጥም በአሁኑ ጊዜ ብዙ ጉባኤዎች አዲስን ወንጌል እየተማሩ ነው። ይህ ወንጌል ብዙ ስሞች ይሰጠዋል፤ ለምሳሌ “ጥራው! የእኔ ነው በለው!” ወንጌል፣ “ንጠቅና ያዘው” ወንጌል፣ “የጤናና ሀብት” ወንጌል፣ “የብልጽግና ወንጌል” እና “የአዎንታዊ አዋጅ አስተምህሮ” ናቸው።