ቅድመ ሁኔታ የሌለው ምርጫን ለመቀበል አምስት ምክንያቶች
'ያለ ቅድመ ሁኔታ ምርጫ' ላይ ያቀረብኩት ተቃውሞ ሁሉ ውድቅ የሆነው፣ ሮሜ 9ን ማብራራት ሲያቅተኝ ነው።. ምዕራፉ የሚጀምረው ጳውሎስ ለ አይሁድ ወገኖቹ ሲል የተረገመ እና ከክርስቶስም ተለይቶ የተጣለ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት በማሳየት ነው (ሮሜ 9፥3)። ይህ የሚያሳየው አንዳንድ አይሁዶች እየጠፉ እንደሆነ ነው። ይህም እግዚአብሔር ለአይሁዶች የገባውን የተስፋ ቃል ላይ ጥያቄ ያስነሣል። አልተሳካም ነበር? ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቃል ተሽሮአል ማለት አይደለም” ሲል ይመልሳል (ሮሜ 9፥6)። ለምን አይሆንም?