የትንሣኤው 10 ውጤቶች | መጋቢት 27

ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው። (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥17)

በክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ያገኘናቸውን 10 ነገሮች እንዘርዝር፦

  1.  ዳግም የማይሞት አዳኝ። “ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶአልና፣ ዳግመኛ እንደማይሞት እናውቃለንና፤ ሞት ከእንግዲህ በእርሱ ላይ ጒልበት አይኖረውም” (ሮሜ 6፥9)።
  2. ንሰሓ። “እናንተ በዕንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን፣ የአባቶቻችን አምላክ ከሙታን አስነሣው፤ እርሱም ለእሥራኤል ንስሓንና የኀጢአትን ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ እግዚአብሔር የሁሉ ራስና አዳኝ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው” (ሐዋርያት ሥራ 5፥30-31)።
  3. አዲስ ውልደት። “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን” (1ኛ ጴጥሮስ 1፥3)።
  4. የኅጢአት ይቅርታ። “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢአታችሁ አላችሁ ማለት ነው” (1 ቆሮንቶስ 15፥17)።
  5. መንፈስ ቅዱስ። “ይህን ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ከሞት አስነሣው፤ እኛም ሁላችን ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ካለ በኋላ፣ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ ተቀብሎ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው” (ሐዋርያት ሥራ 2፥32-33)።
  6. ለተመረጥን ለእኛ ኩነኔ አይኖርም። “ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል” (ሮሜ 8፥34)።
  7. የኢየሱስ የግል አብሮነት እና ጥበቃ። “እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴዎስ 28፥20)።
  8. የመጪው ፍርድ ማረጋገጫ። “በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአልና፤ እርሱንም ከሙታን በማስነሣቱ ለሰዎች ሁሉ ይህን አረጋግጦአል” (ሐዋርያት ሥራ 17፥31)።
  9. ከወደፊቱ የእግዚአብሔር ቁጣ መዳን። “ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ” (1ኛ ተሰሎንቄ 1፥10ሮሜ 5፥9)።
  10. የእኛ የራሳችን ከሞት መነሣት። “ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እኛንም ደግሞ ከኢየሱስ ጋር አስነሥቶ ከእናንተ ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን” (2ኛ ቆሮንቶስ 4፥14ሮሜ 6፥48፥111ኛ ቆሮንቶስ 6፥1415፥20)።