“…እግዚአብሔር (ያህዌ) ሩኅሩኅ ቸር አምላክ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ…” (ዘፀአት 34፥6)።
እግዚአብሔር ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ ነው።
ይህን ሳስብ ሁለት ምስሎች ወደ አእምሮዬ ይመጣሉ፦
- የእግዚአብሔር ልብ፣ የማይቋረጥ ፍቅርና ታማኝነት ለዘመናት እንደሚያመነጭ፣ በተራራ ላይ እንዳለ ምንጭ ነው።
- አልያም ደግሞ የእግዚአብሔር ልብ፣ የፍቅርና ታማኝነት እሳት እንደሚያፈልቅ፣ ሁልጊዜም እንደሚንቦጎቦግ እሳተ ገሞራ ነው።
እግዚአብሔር “የበዛ” (ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ) የሚለውን ቃል ሲጠቀም እንድንረዳ የሚፈልገው፣ የፍቅሩ ምንጮች እንደማይደርቁ ነው። ለቀናት፣ ለዓመታት፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከዚህ ምንጭ መጠጣት ትችላላችሁ። ፈጽሞ አይደርቅም።
መንግሥት የገንዘብ እጥረት ሲኖር ገንዘብን እንደሚያትም፣ እግዚአብሔርም እንዲሁ ነው እስከማለት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ሁለቱም የማያቋርጥ ምንጭ አላቸው አይደል? ልዩነት ግን አላቸው። ገንዘብን ለማተም የእግዚአብሔር ግምጃ ቤት በማያልቅ፣ ወርቅ በሆነ ፍቅር ተሞልቷል። መንግሥት ነገ መልካም ነው እያለ ይኖራል፤ እግዚአብሔር ግን ማለቂያ ከሌለው ከመለኮታዊ ምንጩ እየመነዘረ ይሰጣል።
የእግዚአብሔር ሙላት የሚገለጠው በፍጹም መገኘቱ፣ በሉዓላዊ ነፃነቱ እና በሁሉን ቻይነቱ ነው። እርሱ ከታላቅነቱ የተነሣ ምንም ጉድለቱን መሙላት አያስፈልገውም። እንዲያውም የእርሱ ሙላት ለእኛ ለሚያስፈልገን ለኅጢአተኞች ስጦታ በሆነው በክርስቶስ በኩል ይፈስልናል።
በፍጹም መገኘቱ፣ በሉዓላዊ ነፃነቱ እና በሁሉን ቻይነቱ ስለምንተማመን ፍቅሩን እንደምናገኝ እርግጠኞች እንሆናለን።