ወዳጆች ሆይ፤ ይህ አሁን የምጽፍላችሁ ሁለተኛው መልእክት ነው። ሁለቱንም መልእክቶች የጻፍሁላችሁ ቅን ልቦናችሁን እንድታነቃቁ ለማሳሰብ ነው። (2ኛ ጴጥሮስ 3፥1)
ፋሲካ እየተቃረበ ሲመጣ፣ የኢየሱስ ትንሳኤ ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ በማሰብ ምስጋና እና ደስታ ልባችንን ይሙላ። በአድናቆትና በአግራሞት ሆነን እናነቃቃ። አንድ ሰሞን እጅግ ያስገርመን የነበረ ነገር፣ አሁን እንደተራ መቁጠር የዚህ የወደቀው ተፈጥሯችን ርግማን ነው። ሆኖም ግን እውነታው አልተቀየረም። የተቀየርነው እኛ ነን።
መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን ለዚህ ነው። ጴጥሮስ ሁለቱን መልእክቶቹን የጻፈው በማስታወስ እንዲነቃቁ እና እንዲነሳሱ ለማሳሰብ እንደሆነ ይነግረናል።
ስለዚህ እስቲ እኛም በማስታወስ ቅን አዕምሮዎቻችንን እናነቃቃ።
ኢየሱስን ከሞት በማስነሳቱ እግዚአብሔር ምንድን ነው ያደረገው? አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልሶችን እንመልከት።
በኢየሱስ ትንሳኤ ምክንያት ወደ ሕያው ተስፋ ዳግም ተወልደናል።
1ኛ ጴጥሮስ 1፥3-4፦ “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣ . . . እንደገና ወለደን።”
ኢየሱስ ከሞት ስለተነሳ፣ የተፈጠርንለት ክብር አሁን የእርሱ ሆኗል። የመጨረሻው ዕጣችን እሱን ከነሙሉ ክብሩ እና ማዕረጉ ማየት ነው።
1ኛ ጴጥሮስ 1፥21፦“ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ።”
ዮሐንስ 17፥5፣24፦ “እንግዲህ አባት ሆይ፤ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ጋር በነበረኝ ክብር በአንተ ዘንድ አክብረኝ።
… “አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ፣ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ።”
ከሙታን የተነሣው ጌታ ኢየሱስ ራሱ ቅን አእምሮአችሁን ጥልቅ ወደሆነ አዲስ አምልኮ፣ መሰጠት እና ደስታ እንዲያነቃቃላችሁ እጸልያለሁ።