አስቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው፤ የጠራቸውን አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውን አከበራቸው (ሮሜ 8፥30)።
ከዘላለም በፊት በነበረው በእግዚአብሔር ቅድመ ውሳኔ እና ለዘላለም በሚኖረው በእግዚአብሔር ማክበር መካከል አንድም ነፍስ አይጠፋም።
ለልጅነት አስቀድሞ ከተወሰኑት መካከል ሳይጠራ የሚቀር የለም። ከተጠሩት ከእነዚያ ደግሞ ማንም ከመጽደቅ አይጎድልም። የጸደቀ ደግሞ ሳይከብር አይቀርም። ይህ የመለኮት ኪዳን ታማኝነት ለዘላለም የማይበጠስ ሰንሰለት ነው።
ስለዚህም ጳውሎስ እንዲህ ይላል፦
በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ (ፊልጵስዩስ 1፥6)።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትገኙ እርሱ እስከ መጨረሻው ድረስ አጽንቶ ይጠብቃችኋል። ወደ ልጁ፣ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥8-9)።
ሊዋሽ የማይችለው አምላካችን እነዚህን ተስፋዎች ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ታማኝ በሆነበት በዚያው ልክ፣ ዳግም የተወለዱት ዘላለማዊ መዳንም እንዲሁ የተረጋገጠ ነው።