ታምኑ ዘንድ | ታሕሳስ 26
"ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል።”
"ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል።”
"ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።"
"የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያቢሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።"
"እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሀት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።"
ገና ለሚሲዮን (ወይም ለሚሽነሪነት) ሥራ የሚጠቅም ሞዴል ነው። ሚሲዮናዊነት የገና ነጸብራቅ ነው። “ልክ እንደ እኔ፣ እናንተም” የሚል ሐሳብ እናገኝበታለን።
እግዚአብሔር ቅዱስ እና ፍትሐዊ አምላክ ሲሆን፣ ከእንደኛ ዐይነት ኀጢአተኞች ፍጹም የተለየ ነው። በገናም ጊዜ ሆነ በዓመቱ የትኛውም ወቅት ዋና ችግር የሚሆንብን ነገር ይህ ነው። እጅግ ቅዱስ እና ፍጹም ፍትሐዊ ከሆነ አምላክ ጋር እንዴት እንታረቅ?
የእግዚአብሔር ስኬታማ ውድቀት መጀመሩ የተበሰረው በገና ነው። ኀይሉን ማሳየት የሚወደው ሽንፈት በሚመስል መንገድ ነው። ስትራቴጂያዊ ድሎችን ለመጎናጸፍ ስልታዊ ማፈግፈግን ይተገብራል።
"ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።"