ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ። (የማርቆስ ወንጌል 14፥26)
ኢየሱስ ሲዘምር ይሰማችኋል?
ድምጹ ወፍራም ነበር ወይስ ቀጭን? ይስረቀረቅ ነበር ወይስ ጥርት ያለ ድምጽ ነበረው?
ሲዘምርስ ዓይኑን ጨፍኖ ለአባቱ ነበር? ወይስ የደቀ መዛሙርቱን ዓይን እየተመለከተ በጥልቅ ወዳጅነታቸው ፈገግ ብሎ ነበር?
በአብዛኛው መዝሙሩን የሚጀምረውስ እርሱ ነበር? ወይስ ጴጥሮስ? ወይስ ያዕቆብ? ምናልባትም ማቴዎስ ይሆናል።
ኢየሱስ ሲዘምር ለመስማት አቤት እንዴት ጓጉግቻለሁ! ድምፁን በአጽናፈ ዓለማችን ውስጥ ቢያሰማ ፕላኔቶች ከምህዋራቸው የሚፈነጥቁ ይመስለኛል። ነግር ግን የማይናወጥ መንግሥት አለን፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ ጀምር! አድርገው! ዘምር!
ክርስትና የሚዘምር እምነት ከመሆን ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። መስራቹ ዘምሯልና። መዘመርን ደግሞ የተማረው ከአባቱ ነው። በእርግጠኝነት ከዘላለም በፊት ጀምሮ አብረው ሲዘምሩ ኖረዋል። አይመስላችሁም? በሥላሴ ኅብረት ውስጥ ያለው የማያልቅ ዘላለማዊ ደስታ አይዘምርምን?
መጽሐፍ ቅዱስ የዝማሬያችን ዓላማ “የደስታ ዜማዎችን ” ማዜም እንደሆነ ይነግረናል (1ኛ ዜና መዋዕል 15፥16)። በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ደግሞ ከእግዚአብሔር የበለጠ ደስታ ያለው ማንም የለም። እርሱ ያለገደብ ደስተኛ ነው። ደግሞም በልጁ አምላክነት በኩል በተንጸባረቀው ፍጽምናው እንዳየነው፣ ከዘላለም በፊት ጀምሮ እርሱ ተደስቷል።
የእግዚአብሔር ደስታ ሊታሰብ የማይችልና ኃያል ነው። እርሱ እግዚአብሔር ነው። እርሱ ሲናገር የከዋክብት ክምችት ተፈጥረዋል። ታዲያማ ለደስታ ሲዘምር፣ በአጽናፈ ዓለም ጉዳዮች እና እንቅስቃሴዎች ሁሉ ላይ እንዴት ያለ ኃይል ይወጣ ይሆን?
እግዚአብሔር በእርሱ ያለንን የልብ ደስታ ለመግለጽ መዝሙርን የሰጠን፣ አምሳያው በሆነው ልጁ ያለውን የልብ ደስታ በመንፈሱ በመዘመር መግልጽ፣ እንዴት ያለ ደስታን እንደሚሰጠው ስለሚያውቅ አይመስላችሁም? ታዲያማ የሚዘምር አምላክ ልጆች ስለሆንን፣ እኛም ዘማሪ ሕዝብ ነን።