ስለ እናንተ በተቀበልሁት መከራ አሁንም ደስ ይለኛል፤ ክርስቶስ ስለ አካሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ከተቀበለው መከራ የጐደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ። (ቆላስይስ 1፥24)
ክርስቶስ ለኃጢያተኞች መከራን በመቀበልና በመሞት ለዓለም የፍቅር መስዋዕትን አቅርቧል። መስዋዕትም ፍጹም ነበረ። ለሕዝቡ ሁሉ፣ ሁሉንም ኃጢአት፣ ሙሉ በሙሉ ይከፍላል። የተሻለ ስጦታ ለማድረግ ምንም ነገር መጨመር አይቻልም። አንዳች አይጎድለውምና። ነገር ግን ራሱ ክርስቶስ ለዓለም ህዝቦች ይህንን በልዩ መንገድ ማቅረብ አስፈለገው።
ለዚህም ጉድለት የእግዚአብሔር ምላሽ የክርስቶስን ህዝቦች (እንደ ጳውሎስ ያሉ ሰዎች)፣ የክርስቶስን መከራዎች በየግል ለዓለም እንዲያቀርቡ መጥራት ነው። ይህን ስናደርግ፣ “በክርስቶስ መከራ የጎደለውን እንሞላለን”። የክርስቶስ መከራ የወጠነውን ዕቅድ እኛ እንፈጽማለን። ይህ ውጥን የመከራውን ታላቅ ዋጋ ለማያውቁት ሰዎች የቀረበ ነው።
ነገር ግን በቆላስይስ 1፥24 ላይ ያለው በጣም የሚያስደንቀው ነገር፣ ጳውሎስ በክርስቶስ መከራ የጎደለውን እንዴት እንደሚሞላ ነው።
የክርስቶስን መከራ የሚሞላው በራሱ መከራ እንደሆነ ይናገራል። ይህ ማለት እንግዲህ ጳውሎስ ለክርስቶስ ሊማርካቸው ለሚሞክራቸው ሰዎች ራሱን በማሰቃየት የክርስቶስን መከራ ያሳያል። በ ጳውሎስ መከራ ውስጥ የክርስቶስን መከራ ያያሉ።
አስደናቂው መደምደሚያ ይህ ነው፦ እግዚአብሔር የክርስቶስን መከራ በክርስቲያኖች መከራ በኩል ለዓለም እንዲቀርብ ወዷል።
ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ፣ አካሉ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እንድትቀምሰው እግዚአብሔር ይፈልጋል። ይህም፣ “መስቀሉ ወደ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ነው” ብለን ስናውጅ፣ ሰዎች የመስቀሉን ሰንበር ከላያችን ላይ እንዲመለከቱ እና የመስቀሉን ፍቅር ከእኛ እንዲረዱ ይጋብዛል።