ኢየሱስም አያቸውና፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል” አላቸው። (ማርቆስ 10፥27)
ዓለም ዓቀፍ ክርስቲያን ለመሆን እና ራስን ለወንጌል ተልዕኮዎች ለመስጠት ከኢየሱስ የተሰጡ ሁለት ታላላቅ ማበረታቻዎች እነዚህ ናቸው – እንደ ሂያጅ አልያም እንደ ላኪ።
- በሰው ዘንድ አይቻልም የተባለ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል (ማርቆስ 10፥27)። የደነደኑ ኃጢአተኞች መለወጥ፣ የእግዚአብሔር ሥራ ነው። ያም ደግሞ ከሉዓላዊ ዕቅዱ ጋር የሚስማማ ይሆናል። ስለ ድካማችን መፍራት ወይም መጨነቅ የለብንም። ጦርነቱ የጌታ ነው፣ ድሉንም ይሰጣል።
- ክርስቶስ ለእኛ እንደሚሠራ ቃል ገብቷል፣ ከዚያም የተነሳ የአገልግሎት ህይወታችን ማብቂያ ላይ አንዳች መስዋዕትነትን ከፍለናል ማለት አንችልም (ማርቆስ 10፥29-30)።
እርሱ የሰጠውን የሚስዮናዊነት ትዕዛዝ ስንከተል፣ የሚያሙት የጎንዮሽ ጉዳቶች እንኳ ሳይቀሩ፣ ያለንበትን ሁኔታ የተሻለ ለማድረግ እንደሚሰሩ እንገነዘባለን። መንፈሳዊ ደህንነታችን፣ ደስታችን በመቶ እጥፍ ይሻሻላል። ስንሞትም እንኳ አንሞትም። የዘላለም ህይወትን እናገኛለን።
ይህን ስል ድፍረታችሁንና ለክርስቶስ የምታደርጉትን መስዋዕትነት እንድታቆሙ መጠየቄ አይደለም። ያላችሁን ሁሉ በመካድ፣ የውስጥ ጥልቅ ፍላጎታችሁን የሚያረካ ህይወት እንዲኖራችሁ ነው የምለምነው። ለንጉሰ ነገስቱ አገልግሎት ስትሉ ሁሉንም ነገር እንደ ከንቱ እንድትቆጥሩ ጠይቃችኋለሁ። የገዛችሁትን ልብስ አውልቃችሁ የእግዚአብሔርን የአምባሳደርነት ልብስ እንድትለብሱ እለምናችኋለሁ።
ስደት እና እጦት እንደሚኖር ቃል እገባላችኋለው – ነገር ግን ደስታውን አስታውሱ! “ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና” (ማቴዎስ 5፥10)።
በታህሳስ 29፣ 1948፣ የኢኳዶር አምስት ዋኦራኒ ሕንዶች፣ ጂም ኤሊዮትን እና አራቱን ሚሲዮናውያን ጓደኞቹን፣ ወንጌልን ስልሳ ሰዎች ወዳሉት የዋኦራኒ ነገድ ለማምጣት ሲሞክሩ፣ ገደሏቸው። አራት ወጣት ሚስቶች ባሎቻቸውን፣ ዘጠኝ ልጆች አባቶቻቸውን አጡ። ኤልሳቤጥ ኤሊዮት፣ ዓለም የመከራ ቅዠት ብሎ ጠራው በማለት ጽፋለች። ከዚያም ቀጥላ፣ “ዓለም በጂም ኤሊዮት የእምነት መግለጫ ሁለተኛ ሐረግ ላይ የሚገኘውን እውነት አላስተዋለውም ነበር፦ ‘የማያጣውን ለማግኘት ማቆየት የማይችለውን የሚሰጥ ሞኝ አይደለም።’”