የእግዚአብሔር ዕቅድ ለሰማዕታት | ሐምሌ 28

ከዚያም ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ ወደ ፊት እንደ እነርሱ የሚገደሉ የአገልጋይ ባልንጀሮቻቸውና ወንድሞቻቸው ቊጥር እስኪሞላ ድረስ ጥቂት ጊዜ እንዲታገሡ ተነገራቸው” (ራእይ 6፥11)።

ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል ክርስትና በሰማዕታት ደም በጨቀየ ምድር ውስጥ እያደገ ቆይቷል።

በ98 ዓ.ም ገደማ ትራጃን የተባለ ንጉሥ እስኪነሳ ድረስ ስደት ይፈቀድ ነበር፤ ነገር ግን ሕጋዊ አልነበረም። ከትራጃን እስከ ዴሲየስ (250 ዓ.ም. አካባቢ) ደግሞ ስደት ሕጋዊ ነበር። ክርስቲያኖችን ከሚጠላው እና በተሃድሶዎቹ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ ከፈራው ዴሲየስ ከተባለው ንጉሥ በ311 ዓ.ም. እስከ መጀመሪያው የመቻቻል አዋጅ ድረስ፣ ስደቱ ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ሰፊ እና አስከፊ መልክ ነበረው።

አንድ ጸሐፊ በዚህ በሦስተኛው ክፍለ ጊዜ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ገልጿል፦

ጭካኔ በየቦታው በጉባኤዎች ተሰራጭቶ ነበር፤ ደግሞም ከመከራው የተነሣ እምነታቸውን የካዱ በጣም ብዙ ነበሩ። ነገር ግን ጸንተው በመቆም ከክህደት ይልቅ ሰማዕትነትን የተቀበሉትም ጥቂት አልነበሩም። እንዲሁም ስደቱ እየሰፋ እና እየጠነከረ ሲሄድ፣ የክርስቲያኖች ግለት እና ስደቱን የመቋቋም ኃይላቸው እያደገና እየጠነከረ መጥቷል።

ስለዚህ፣ ለሦስት መቶ ዓመታት ያክል፣ ክርስቲያን መሆን ማለት በሕይወታችሁ፣ በንብረታችሁ እና በቤተሰባችሁ ላይ እጅግ አደገና አደጋን የሚከተለው ድርጊት ነበር። አብልጣችሁ የምትወዱት ነገር ምን መሆኑን የሚያሳይ ፈተና ነበር። ይህ አስከፊ ፈተና ብዙ ጊዜ እስከ ሞት ሰማዕትነት ድረስ ይሄድ ነበር።

አንድ ነገር ግን እናስተውል። ከዚህ ሁሉ ሰማዕትነት በላይ የሆነ ንጉሥ አለ። ሉዓላዊው እግዚአብሔር የወሰናቸው የሰማዕታት ቁጥር እንዳሉ ቃሉ ይነግረናል። እነዚህ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን በመትከልና አቅም በመሆን ረገድ ልዩ ሚና አላቸው። “የእግዚአብሔር ልጆች አምላካቸውን የሚያገለግሉት የተሻለ ሕይወት ስለሚያገኙ ብቻ ነው” እያለ ዕለት ዕለት የውሸት ዲስኩሩን የሚነዛውን የሰይጣንን አፍ በመዝጋት ረገድ ልዩ ሚና አላቸው። የኢዮብ 1፥9-11 ነጥብም ይኸው ነው።

ሰማዕትነት በአጋጣሚ የመጣ አይደለም። ያልተጠበቀ እና እግዚአብሔርን የሚያስደነግጥ ጉዳይም አይደለም። ስለ ክርስቶስ የሚደረግ ሥልታዊ ሽንፈትም በጭራሽ አይደለም።

ሽንፈት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በሰው ስሌት ማንም ሊረዳውና ሊነድፈውና የማይችለው፣ የሰማዩ ዕቅድ አካል ነው። በእግዚአብሔር ጸጋ በማመን እስከመጨረሻው በእምነት ለሚጸኑት ሁሉ ይህ ዕቅድ አሸናፊ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው።