ታላቅ ደስታ የምሥራች

ጆን ፓይፐር

ኑ! ኢየሱስን አብረን እናክብረው። የገና ክብረ በዓል ግቡ ኢየሱስን ለማድነቅ ነው። ሟች ለሆነው ማንነታችን ዘለዓለማዊው አምላክ መምጣቱን እያከበርን፣ ልባችንን ለገና ቀን ክብር የምናዘጋጅበት የዝግጅት ወቅት ነው። ከጆን ፓይፐር የቀረቡላችሁ እነዚህ ሃያ አምስት አጫጭር የጥሞና ንባቦች፣ ዓላማቸው ኢየሱስን የገና ሰሞን ዋና እንድታደርጉ መርዳት ነው።

ስለ ጸሐፊው

ጆን ፓይፐር የዲዛየሪንግ ጋድ እና የቤተልሔም ሥነ መለኮት ኮሌጅ መሥራች እና ዋና አስተማሪ ነው። ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በምትገኘው ቤተልሔም ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጋቢ በመሆን ለሠላሳ ሦስት ዓመታት አገልግሏል። Desiring God፣ Don’t Waste Your Life፣ እና Providence የሚሉትን ጨምሮ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ መጽሐፍትም ደራሲ ነው።

ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 142

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም