የማደርገው ላደርገው የምፈልገውን በጎ ነገር አይደለም፤ ዳሩ ግን ለማድረግ የማልፈልገውን ክፉ ነገር ነው። (ሮሜ 7፥19)
ክርስቲያኖች በሽንፈት ብቻ የሚኖሩ አይደሉም። ነገር ግን ኃጢአትንም ፍጹም ድል አድርገውም አይኖሩም። እናም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት በተሳነን ጊዜ፣ በሮሜ 7፥13-25 ያለው ክፍል ጤናማ ክርስቲያናዊ ምላሽን እንዴት መስጠት እንዳለብን ያሳየናል።
እንዲህ ማለት ይኖርብናል፦
- የእግዚአብሔርን ሕግ እወዳለሁ። (ቁጥር 22)
- አሁን ያደረኩትን ጠልቼዋለሁ። (ቁጥር 15)
- እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል? (ቁጥር 24)
- እግዚአብሔር ይመስገን! በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድሉ ይመጣል። (ቁጥር 25)
በሌላ አነጋገር፣ ማንም ክርስቲያን በሽንፈት መኖር አይፈልግም። ማንም ክርስቲያን ተሸንፎ ለመኖር አይመቻችም። ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜ ከተሸነፍን፣ ስለ መሸነፋችን መዋሸት የለብንም።
ግብዝነትና መደንዘዝ መኖር የለበትም። የሚያስኮራም ፍጹምነት እንደዛው። መንፈሳዊ መምሰል፣ የውሸት ፈገግታ ወይም ላይ ላዩን የሆነ ደስታ ሊኖር አይገባም።
ከዚህም በላይ ደግሞ፣ እግዚአብሔር ለራሳችን ውድቀቶች ጭፍን ከመሆንና ተከትሎት ከሚመጣ በሌሎች ላይ መፍረድ አድኖናል።
እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሌሎች ውድቀት ይልቅ በራሳችን ጉድለት እንድናዝን እርዳን።
እግዚአብሔር ሆይ፣ በዚህ ክፍል ላይ ያለውን የሐዋርያው ጳውሎስን ታማኝነት፣ ቅንነት እና ትህትናውን ስጠን! “እኔ ምን ዐይነት ጐስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል? በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን” (ሮሜ 7፥24–25)።