ከጠራችሁ፣ ያጸናችኋል | መጋቢት 30

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትገኙ እርሱ እስከ መጨረሻው ድረስ አጽንቶ ይጠብቃችኋል። ወደ ልጁ፣ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥8-9)

ኢየሱስ እስከሚመጣ ድረስ እምነታችሁ እንዲጸና ለማድረግ በምን ላይ ትታመናላችሁ? ጥያቄው፣ “በዘላለማዊ ዋስትና ታምናላችሁ ወይ” የሚል ሳይሆን፣ “ለዘለዓለም የምንጸናው እንዴት ነው?” የሚል ነው።

የእምነታችን ጥንካሬ በራሳችን ባለን መተማመን ላይ ብቻ ነው የሚደገፈው? ወይስ እግዚአብሔርን ማመን እንድንቀጥል በሚሠራው ሥራ ላይ የቆመ ነው?

እግዚአብሔር የጠራቸውን እስከ መጨረሻው ድረስ አጽንቶ እንደሚጠብቅ መናገሩ ታላቅ የቃሉ እውነታ ነው። ለዘላለም የተጠበቅን መሆናችን ላይ ያለን እምነት እግዚአብሔርን ማመን እንድንቀጥል እንደሚደግፈን ያሳየናል።

ዘላለም እርግጥ እንደሆነው ሁሉ፣ እግዚአብሔር በማመን መቀጠላችንም እርግጥ ነው። ለጠራቸው ደግሞ ይሄ እውነት በጣም እርግጥ ነው።

ሦስት ጥቅሶች የእግዚአብሔርን ጥሪ እና ጥበቃ እንደዚህ ያስቀምጡታል፦

  1. “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትገኙ እርሱ እስከ መጨረሻው ድረስ አጽንቶ ይጠብቃችኋል። ወደ ልጁ፣ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው“ (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥8-9)።
  2. “የሰላም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ያለ ነቀፋ ይጠበቁ። የጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ያደርገዋል“ (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥23-24)።
  3. “የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፤ ለተጠሩት፣ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቁት፤ ምሕረት፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ“ (ይሁዳ 1፥2)። (ተመሳሳይ ጥቅሶችን በሮሜ 8፥30ፊልጵስዩስ 1፥61ኛ ጴጥሮስ 1፥5ይሁዳ 4 ላይ ታገኛላችሁ)።

የእግዚአብሔር “ታማኝነት” የጠራቸውን ሁሉ ለዘላለም እንደሚጠብቃቸው ያረጋግጥልናል።