በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ኃይል ላይ በመተማመን ኑሩ | መስከረም 20

ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነው ኀይሉ… (ኤፌሶን 1፥19)።

የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ማለት፣ በዚህ ምድር ላይ ሁኔታዎች ቢቀያየሩ እንኳ ዘላለማዊ በሆነ እና በማይናወጥ የእግዚአብሔር ክብር ውስጥ መሸሸግ ማለት ነው። ይሄ መተማመኛ ለእግዚአብሔር ጥሪ በፍጹም መታዘዝ እንድንችል አቅም ይሆነናል።

በዕለት ተዕለት ኑሯችን፣ በተለመደው ሆነ በልዩ ልዩ የሕይወት ገጠመኞች መካከል፣ “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መጠጊያህ ነው” ከሚለው እውነት የተሻለ ነፃ የሚያወጣ፣ የሚያስደስት ወይም ይበልጥ ጉልበት የሚሰጥ ነገር ከየት ይገኛል?

ይህንን ካመንን፣ ይህ የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እውነት አጥብቆ እንዲይዘን ከፈቀድን፣ በግል ሕይወታችን እና በአገልግሎታችን ላይ ምን ያህል ለውጥ ያመጣ ይሆን!? ለእግዚአብሔር የማዳን አጀንዳ ምንኛ ትሑት እና ብርቱ እንሆናለን!

የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ማለት ለእግዚአብሔር ሕዝብ መሸሸጊያ ማለት ነው። መሸሸጊያችሁ የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት መሆኑን ስታምኑ ደግሞ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ በታዛዥነት ሕይወት ውስጥ እንደ ወንዝ የሚፈስ ደስታ፣ ነፃነት፣ እና ኅይል አለ።

የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ማለት ለቃል ኪዳኑ ሕዝብ ክብር፣ ብድራት እና መሸሸጊያ ማለት ነው። የጸጋውን ቃል ኪዳን እንድትቀበሉ እጋብዛችኋለሁ፦ ከኃጢአት ተመለሱ! በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ! ደግሞም ሁሉን ቻይ የሆነው የእግዚአብሔር ኃያልነት ለነፍሳችሁ ክብር፣ ለጠላቶቻችሁ ብድራት እና ለሕይወታችሁ መሸሸጊያ ይሆናል።