የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም። (ኢሳይያስ 42፥3)
ምናልባትም በቅርቡ ከሰማኋቸው እጅግ አበረታች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ዋነኛው ኢሳይያስ 42፥1-3 ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ኢየሱስ መንፈሳዊ ኅይሉን እንዴት እንደሚጠቀም ያሳየናል።
“የተቀጠቀጠ ሸምበቆ” የሆናችሁ ያህል ይሰማችኋል? ልክ ከክብደታቸው የተነሣ ግንዳቸው ተሰብሮ ምግብ እንደማያገኙት እና እንደወደቁት አበቦች ወይም ደግሞ ልክ እሳቱ እንደጠፋ እና በጥቂቱ እንደሚብለጨለጭ የልደት ሻማ የሆናችሁ ይመስላችኋል?
ልብ በሉ! የክርስቶስ መንፈስ የሚያበረታ መንፈስ ነው። አበባችሁን አይቆርጥም፤ ብልጭ ያለች እሳታችሁን አያጠፋም።
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው… ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ“ (ሉቃስ 4፥18)። “ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሓይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች“ (ሚልክያስ 4፥2)። “እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ“ (ማቴዎስ 11፥29)። “እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፣ በርታ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ“ (መዝሙር 27፥14)።
ብልጭ የምትል ትንሽ እሳት እንጂ የሚንቦገቦግ እሳት አለመሆናችን ሊያሳዝነን ይችላል። ግን ስሙኝ! በብልጭታ እና በእሳት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። በአንጻሩ ደግሞ በብልጭታ እና በጨለማ መካከል እጅግ ሰፊ ልዩነት አለ! አንዲት ቅንጣት የእምነት ፍሬ ከመጥፋት ይልቅ ተራራ ወደሚያክል እምነት ለመቀየር ቅርብ ናት!
ለእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች በራችሁን ክፈቱና መንፈሱ ወደ ልባችሁ እንዲገባ ፍቀዱለት። የእግዚአብሔር ቅዱስ ነፋስ የሚያጠፋም የሚሰብርም አይደለም። ቀና ያደርጋችኋል፤ ሊጠፋ ያለውን እሳት ቦግ ያደርገዋል። እርሱ የሚያበረታ መንፈስ ነውና።