ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ሲል ቤቱን ወይም ወንድሞቹን ወይም እኅቶቹን ወይም እናቱን ወይም አባቱን ወይም ልጆቹን ወይም ዕርሻውን የተወ ሁሉ፣ አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ እናቶችን፣ ልጆችንና ዕርሻን መቶ ዕጥፍ የማይቀበል፣ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይወርስ የለም። (ማርቆስ 10፥29-30)
ኢየሱስ እዚህ ጋር ለየትኛውም መሥዋዕትነት እኔ ጋር የካሳ ክፍያ አለ እያለ ነው።
- አጠገባችሁ ያለውን የእናታችሁን ፍቅር እና እንክብካቤ አሳልፋችሁ ከሰጣችሁ፣ በመቶ እጥፍ የሚበልጠውን የክርስቶስን የዘላለም ፍቅር ታገኛላችሁ።
- የወንድማችሁን የሞቀ ጓደኝነት አሳልፋችሁ ከሰጣችሁ፣ በመቶ እጥፍ የሚበልጠውን የክርስቶስን የሞቀ ወዳጅነትን ታገኛላችሁ።
- የሞቀ ቤታችሁን አሳልፋችሁ ከሰጣችሁ፣ በመቶ እጥፍ የሚበልጠውን፣ ሁሉ ቤት የእርሱ የሆነውን የአምላካችሁን ምቾት እና ጥበቃ ታገኛላችሁ።
ለመላክ ለተዘጋጁት ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ እያላቸው ያለው እንዲህ ነው፦ “ይህንን ያንን መስዋዕት አድርጌአለሁ ብላችሁ ለማናገር እስከማትደፍሩ ድረስ ለእናንተ ለመትጋት እና ከጎናችሁም ለመሆን ቃል እገባለሁ።”
ኢየሱስ ለጴጥሮስ “የመሥዋዕትነትን ጀብድ” የነበረው ምላሽ ምን ነበር? ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ” (ማርቆስ 10፥28)። ይህ በኢየሱስ ተቀባይነት ያለው ራስን የመካድ መንፈስ አይደለም።
ኢየሱስ ለጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ማንም ለኔ መቶ እጥፍ መልሼ የማልከፍለውን ነገር መሥዋዕት አያደርግልኝም – በዚህም ሆነ በሚመጣው ዘላለማዊ ዓለም።”