ሦስት የገና ስጦታዎች | ታሕሳስ 29
ይህንን አስደናቂ ሁኔታ ከእኔ ጋር አብራችሁ አብሰልስሉ። የእግዚአብሔር ልጅ የመጣው ኀጢአት መሥራት እንድታቆሙ ሊረዳችሁ፣ የዲያቢሎስን ሥራ ሊያፈርስ፣ እና ኀጢአት ስትሠሩ ደግሞ ሊያስተሰርይላችሁና የእግዚአብሔርን ቁጣ ከላያችሁ ሊያነሣ ከሆነ፣ ይህ እውነት ሕይወታችሁን ለመኖር ምን ዐይነት አንድምታ ይኖረዋል? ምንስ ይሰጠናል?

በአንደኛ ዮሐንስ 3፥8 “የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው” ሲል ስለ የትኛው የዲያቢሎስ ሥራ እያወራ ነው ያለው? መልሱ ከአውዱ ግልጽ ነው። በመጀመሪያ፣ 1ኛ ዮሐንስ 3፥5 ግልጽ የሆነ ማስተያያ ነው።
"የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን።"
"ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል።”
"ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።"
"የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያቢሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።"
"እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሀት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።"
ገና ለሚሲዮን (ወይም ለሚሽነሪነት) ሥራ የሚጠቅም ሞዴል ነው። ሚሲዮናዊነት የገና ነጸብራቅ ነው። “ልክ እንደ እኔ፣ እናንተም” የሚል ሐሳብ እናገኝበታለን።