ስለ መለወጥ ያለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምን ዐይነት ተግባራዊ ለውጥ ያስከትላል?
ስለ መለወጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ያላት ቤተክርስቲያን እና የሌላት ቤተክርስቲያን መካከል ያለው የግንዛቤ ልዩነት ምን ይመስላል?
0 Comments
ስለ መለወጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ያላት ቤተክርስቲያን እና የሌላት ቤተክርስቲያን መካከል ያለው የግንዛቤ ልዩነት ምን ይመስላል?
የወንጌል ስብከትንና ቤተክርስቲያንን የሚያገናኝ ትልቅ ምስል አለ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የመጀመሪያ ምዕራፎች ያስተዋለን ከሆነ፣ ሐዋሪያቱ ትንሣኤውን ሲሰብኩ ከጀርባ ደግሞ በጋራ የሚኖሩ፣ ያላቸውን በአንድነት ያደረጉና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰዎች መሃከል በሞገስ የሚመላለሱ ሰዎች ያሉባት ቤተክርስቲያን ነበረች (2፥47፤ 5፥13)። በሆነ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ከወንጌል ስብከት ጀርባ እንደ ምስክር ሆኖ ያገለግላል። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ቅዱሳንን በሞገስ እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል፤ ብዙዎችንም ወደ ድነት የመራ ይመስላል።