ልጆችን እየገደሉ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን
በአንድ ወቅት ውርጃን የሚደግፍን አንድ ሰው፣ ፅንሶች እንዴት የሰው ልጆች እንደሆኑ ዐሥር ምክንያቶች ልሰጠው ተዘጋጅቼ ምሳ ልጋብዘው ወጣን። አስቆመኝና፣ “ልጆች እየገደልን እንደሆነ አውቃለሁ” አለኝ። እጅግ በጣም ደነገጥሁ። ቀጠለና፣ “ለሴቶች ጉዳዩ የፍትሕ ነው። ከሁለቱ ክፉ ነገሮች የከፋው የሚሆነው ሴቶችን የሥነ ተዋልዶ ነፃነት መንፈግ ነው” አለ።