ወርቅ፣ ከርቤ፣ እና ዕጣን | ታሕሳስ 14

እግዚአብሔር አንዳች ነገር እንደሚጎድለው በሰዎች እጅ አይገለገልም (ሐዋርያት ሥራ 17፥25)። የሰብዓ ሰገል ስጦታዎች የቀረቡለት እርዳታ ስለሚያሻው ወይም የሚጎድለው ነገር ስለነበር አይደለም። . . . ታዲያ ትርጉማቸው ምንድን ነው? እንዴት ነው አምልኮ የሚሆኑት?

0 Comments
ለኢየሱስ ሁለት ዐይነት ተቃውሞዎች | ታሕሳስ 13

ኢየሱስን ሊያመልኩ የማይፈልጉ ሰዎች በእርሱ ይታወካሉ፤ ሊያመልኩት በወደዱ ላይ ደግሞ ተቃውሞ ያስነሣባቸዋል። ምናልባት የማቴዎስ ዋነኛ ነጥብ ይህ ሐሳብ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ታሪኩ ሲቀጥል ልናመልጠው የማንችለው ወሳኝ አንድምታ ነው።

0 Comments
እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን | ታሕሳስ 10

ሰላም ለእነማን? በመላእክቱ ውዳሴ ውስጥ ጠንከር ያለ እውነታ አለ። እግዚአብሔር ለወደዳቸው ሰዎች ሰላም ይሁን። እርሱ ለሚደሰትባቸው ሰዎች ሰላም ይሁን። ነገር ግን ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም (ዕብራውያን 11፥6)። ስለዚህም የገና በዓል ለሁሉም ሰው ሰላምን ሊያመጣ አይችልም።

0 Comments
ለረጅም ጊዜ የተጠበቀው ጉብኝት | ታሕሳስ 7

"የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤ ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው።"

0 Comments