በዘመናችን ያለው የአብዛኛው ስብከት ችግር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ-መለኮት እንደ መፍትሔ
አብዛኛውን ጊዜ ስብከቶች የሚያተኩሩት፣ የተሳካ ትዳር ለመመሥረት ወይም በባሕላችን ልጆችን ማሳደግ የሚቻልበት መንገድ ላይ ነው። በርግጥ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ስብከቶች ተስማሚ እና አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሁለት ችግሮች ይከሰታሉ። በመጀመሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ እነዚህ ጉዳዮች የሚናገሩት ነገር በአብዛኛው ችላ ይባላል። ምን ያህሎቹ ስብከቶች ጳውሎስ ስለ ወንዶች እና ሴቶች ሚና ምን እንደሚል በታማኝነት እና በአስፈላጊ ጊዜ ይናገራሉ (ኤፌሶን 5፥22-33)? ወይስ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚናገሩት እናፍራለን? ሁለተኛ፣ እና ምናልባትም ከዚ በከፋ ሁኔታ፣ እንደዚህ ዐይነት ስብከቶች የሚሰበኩት (ሁልጊዜም ማለት ይቻላል) በአግድመት ደረጃ (horizontal level) ነው።
0 Comments