“ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ፤ ብፁዓን ናችሁ” (ማቴዎስ 5፥11)
“ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ” (ሉቃስ 10፥20)።
ኢየሱስ ደስታችንን ከመከራና ከስኬት ሥጋት የምንጠብቅበትን ምስጢር ገልጾልናል። ምስጢሩም ይህ ነው፦
በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ነው። የዚያ ዋጋ መጨረሻም የኢየሱስ ክርስቶስን የክብር ሙላት ማጣጣም ነው (ዮሐንስ 17፥24)።
ኢየሱስ ደስታችንን ከመከራ እንዲህ ሲል ይጠብቃል፦
“ሰዎች በእኔ ምክንያት ቢሰድቧችሁ፣ ቢያሳድዷችሁና ክፉውን ሁሉ በሐሰት ቢያስወሩባችሁ፤ ብፁዓን ናችሁ። በሰማይ የምትቀበሉት ዋጋ ታላቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት እንደዚሁ አሳደዋቸዋልና” (ማቴዎስ 5፥11-12)።
በሰማይ የምንቀበለው ታላቁ ሽልማት፣ ደስታችንን ከስደትና ከስድብ ሥጋት ይጠብቅልናል።
በተጨማሪ ደስታችንን ከስኬት እንዲህ በማለት ይጠብቃል፦
“ይሁን እንጂ መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ” (ሉቃስ 10፥20)።
ደቀ መዛሙርቱ ደስታቸውን በአገልግሎት ስኬት ላይ ለማድረግ ተፈትነው ነበር። “ጌታ ሆይ፤ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዙልን” (ሉቃስ 10፥17)። ይህ ግን ደስታቸውን ብቸኛው መልሕቃቸው ከሆነው ኢየሱስ ይለየው ነበር።
ስለዚህም ኢየሱስ በሰማይ ያለውን የበለጠውን ሽልማት በማሳየት ደስታቸውን ከስኬት ሥጋት ጠብቆላቸዋል። በዚህ ደስ ይበላችሁ፦ ስማችሁ በሰማይ ተጽፏል። ውርሳችሁ ገደብ የለውም፣ ዘላለማዊና የተረጋገጠ ነው።
ደስታችን የተጠበቀ ነው። ስደትም ሆነ ስኬት መልሕቁን ሊበጥሱ አይችሉም። በሰማይ የሚጠብቃችሁ ሽልማት ታላቅ ነው። ስማችሁ በዚያ ተጽፏል። የተረጋገጠ ነው።
ኢየሱስ የሚሰደዱ ቅዱሳን የደስታ መሠረታቸው በሰማይ ሽልማት ላይ እንዲሆን አድርጎታል። የስኬታማ ቅዱሳንንም ደስታ እንደዚሁ።
በዚህም ከምድራዊ ሕመምና ደስታ፣ ከዓለማዊ መከራ እና ስኬት ነፃ አውጥቶናል።