የልምምድ ቁልፍ | ጥር 12

“ሁልጊዜ በሁሉ ነገር የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ እንድትተርፉ፣ እግዚአብሔር ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።” (2ኛ ቆሮንቶስ 9፥8)

በእግዚአብሔር የወደፊት ጸጋ ማመን በጎነትን የመለማመድ ቁልፍ እንደሆነ እናውቃለን፤ ምክንያቱም ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ ይህን ታላቅ ቃል ኪዳን ያሳየናል፦ “ሁል ጊዜ በሁሉ ነገር የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ እንድትተርፉ፣ እግዚአብሔር ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል” (2ኛ ቆሮንቶስ 9፥8)። በሌላ አባባል ያለንን ገንዛብ በሙሉ ለማስቀመጥ ከመፈለግ ነፃ መሆን ያስፈልገናል፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ (በጸጋ) መትረፍረፍ ከፈለግን እምነታችንን በወደፊት ባለው ጸጋ ላይ እናድርግ። ለዚህ ምክንያት ወደፊት ባሉት ጊዜያት በሙሉ “እግዚአብሔር ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል” የሚለውን ቃል እንመን።

በወደፊት ባለው ጸጋ ያለንን እምነት በጎነትን “የመለማመድ ቁልፍ” ብዬዋለሁ። የልምምድ ቁልፍ አለ፤ የታሪክም ቁልፍ አለ። ስለተቀበሉት ጸጋ ሲያወራ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎችን ስለታሪክ ቁልፍ ያስታወሳቸዋል፦ “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ” (2 ቆሮንቶስ 8፥9)።

ያለዚህ ታሪካዊ የጸጋ ሥራ ክርስቶስን የሚያከብረው በጎነት በር ዝግ ይሆን ነበር። ይህ ያለፈ ጸጋ የማይተው የፍቅር ቁልፍ ነው።

ነገር ግን ይህ ያለፈ ጊዜ ጸጋ እንዴት እንደሚሠራ እንመልከት። የወደፊት ጸጋን (ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ) መሠረት (ድኻ ሆነ) ያስቀምጣል። የበጎነት ታሪካዊ ቁልፍ የሚሠራው የመለማመድን ቁልፍ መሠረት በወደፊቱ ጸጋ ላይ በማስቀመጥ ነው።

ስለዚህም ፍቅር እና በጎነትን የመለማመድ ቁልፍ ይህ ነው፤ እምነታችሁን በወደፊቱ ጸጋ ላይ አድርጉ፤ በሁሉ ነገር የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችሁ በጎ ሥራን ትወዱ ዘንድ “እግዚአብሔር (የወደ ፊት) ጸጋን ሁሉ (ወደ ፊት) ሊያበዛላችሁ ይችላል።”

ከመስገብገብ ነፃ የሚኮነው እምነታችንን በእግዚአብሔር የወደ ፊት ጸጋ ላይ በማድረግ ነው።