ብቸኛውና እውነተኛው ነፃነት | መስከረም 12

ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ… ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ። (1ኛ ጴጥሮስ 3፥10-11)

እውነተኛ ነፃነት ምንድን ነው? በርግጥ ነፃ ናችሁን?

ሙሉ በሙሉ ነፃ ለመሆን ከፈለግን እነዚህ አራት ነገሮች የግድ ያስፈልጋሉ።

  1. አንድን ነገር ለማድረግ ፍላጎት ከሌላችሁ፣ ያንን ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ነፃ አይደላችሁም። ማድረግ የማትፈልጉትን ለማድረግ ራሳችሁን ልታስገድዱ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ማንም ቢሆን ይህንን ሙሉ ነፃነት አይለውም። ለመኖር የምንፈልገው እንደዚህ አይደለም። በእኛ ላይ የማንፈልገው ገደብ እና ጫና አለ።
  2. አንድ ነገር ለማድረግ ፍላጎት ኖሯችሁ፣ ለማድረግ ግን ችሎታ ከሌላችሁ፣ ያንን ለማድረግ ነፃ አይደላችሁም።
  3. አንድን ነገር ለማድረግ ፍላጎት እና ችሎታ ኖሯችሁ፣ ነገር ግን ለማድረግ ዕድል ከሌላችሁ፣ ያንን ለማድረግ ነፃ አይደለችሁም።
  4. አንድን ነገር ለማድረግ ፍላጎት፣ ችሎታና ዕድል ኖሯችሁ፣ ያንን ማድረግ ግን በስተ መጨረሻ የሚያጠፋችሁ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ ነፃ አይደላችሁም።

ጸጸት የሌለበት ዘላቂ ደስታ የሚሰጡንን ነገሮች ለማድረግ ፍላጎቱ፣ አቅሙ እና ዕድሉ ካለን ሙሉ በሙሉ ነፃ ነን ማለት ነው። ይህንንም ሊያደርግልን የሚችለው ስለ እኛ የሞተውና የተነሣው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ብቻ ነው።

“እንግዲህ ወልድ ነፃ ካወጣችሁ፣ በእውነት ነፃ ትሆናላችሁ” (ዮሐንስ 8፥36)።