ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል። (ኢሳይያስ 25፥3)
ኢሳይያስ ከእያንዳንዱ ወገን የተወጣጡ የዓለም ሕዝቦች፣ የእስራኤል እና የመሲሑ አምላክ ከሆነው ከያሕዌ ጋር የማይጋጩበት ቀን እንደሚመጣ አይቷል።
ከእንግዲህ ወዲህ በዓልን ወይም ሞሎክን ወይም አላህን ወይም ቡድሃን አያመልኩም። ይልቅ በተራራ ላይ ወዳለው የእግዚአብሔር ግብዣ በእምነት ይመጣሉ።
የሐዘን ጭምብል ከፊታቸው ላይ ይወገዳል፤ ሞት ይዋጣል፤ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኅፍረታቸው ይወገዳል፤ እንዲሁም እንባቸው ይታበሳል።
ኢሳይያስ 25፥3ን ለመረዳት ይህ ሊገባን ይገባል፦ “ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።” በሌላ አባባል፣ እግዚአብሔር ከ”ብርቱ ሕዝቦች” በላይ ብርቱ ነው፤ ደግሞም ኅያል እና መልካም ከመሆኑ የተነሣ ጨካኝ ሕዝቦችም እንዲያከብሩት ያደርጋል።
ስለዚህ ኢሳይያስ የሚገልጽልን፣ በአምልኮ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱ ሕዝቦችን፣ ለሰዎች ሁሉ የቀረበ ታላቅ ድግስን፣ ከሕዝቦች ላይ የተወገደ ሐዘን እና ሃፍረትን፣ እንዲሁም የሞትን ለመጨረሻ ጊዜ መወገድ ነው።
ይህ ድል የተረጋገጠ ነው፤ ምክንያቱም ፈፃሚው እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ምንም ሊያጠራጥረን አይገባም።
ወንጌልን በመስበክ ያለፈ አንድም ሕይወት በከንቱ አልባከነም፤ ለመንግሥቱ ማስፋፊያ የዋለ የትኛውም ጸሎት፣ ብር ወይም ማበረታቻ አንዱም በከንቱ አልባከነም።
ድሉ የተረጋገጠ ነው።