ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ (መዝሙር 103፥1)።
ይህ መዝሙር የሚጀምረውም ሆነ የሚጨርሰው፣ ዘማሪው ነፍሱን እያዘዛት ነው፦ “ ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ” ይላታል። እርሱ ብቻ ሳይሆን ደግሞ መላእክት፣ የሰማይ ሠራዊት ሁሉና የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ሁሉ ይህንኑ መባረክ እግዚአብሔርን እንዲባርኩ ይሰብክላቸዋል።
እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤
ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤
እግዚአብሔርን ባርኩ።
እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፤
ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ።
እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣
ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ፤
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
ይህ መዝሙር እጅጉኑ እግዚአብሔርን በመባረክ ላይ ያተኮረ ነው። ታዲያ እግዚአብሔርን መባረክ ማለት ምን ማለት ነው?
እግዚአብሔርን መባረክ ማለት ስለእርሱ ታላቅነትና መልካምነት ከጥልቅ ከነፍሳችን የእውነት መናገር ማለት ነው።
ዳዊት በመዝሙሩ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ “ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ” ሲል፣ ስለ እግዚአብሔር መልካምነት እና ታላቅነት እውነተኛ የሆነ ንግግር መምጣት ያለበት ከነፍሳችን ነው እያለ ነው።
በአንደበት ብቻ የሆነና ከነፍስ ያልመነጨ እግዚአብሔርን መባረክ ግብዝነት ነው። ኢየሱስ በማቴዎስ 15፥8 “ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው” ብሏል። የዚህን ሁኔታ አደገኝነት ዳዊት ስለተረዳ ለራሱ ይሰብካል። ይህ እንዳይፈጠር ለነፍሱ እየነገራት ነው።
“ነፍሴ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና መልካምነት ተመልከቺ። አንደበቴን ተጠቅመሽ በሁለንተናችን ጌታን እንባርከው። ነፍሴ ሆይ ግብዝ አንሁን፣ እግዚአብሔርን ባርኪ!”