የቤተ ክርስቲያን አባልነት

ጆናታን ሊማን

የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን በክርስትና ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ግን ይዘነጋል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተደራጀ ሃይማኖትን በጽኑ መቃወም እና በተቋም ውስጥ የመሆን ጥላቻ ይስተዋላል።

ጆናታን ሊማን ግልጽ በሆነ ማብራሪያ የቤተ ክርስቲያን አባልነት ምን እንደሆነ እና ለምን እንዳስፈለገ ይዳስሳል። የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ተገቢ ስፍራው እየመለሰ፣ የአጥቢያ አካል ውስጥ ታማኝ የሚኮንበትን አሳማኝ ሙግት ያቀርባል።

ስለ ጸሐፊው

ጆናታን ሊማን (ማስተርስ ኦፍ ዲቪኒቲ፣ ሳውዘርን ባፕቲስት ሥነ መለኮት ሴሚናሪ) በዋሽንግተን ዲሲ የምትገኘው የካፒቶል ሂል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን አባል ሲሆን “The Church and the Surprising offense of God’s Love” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ነው። በ9Marks Ministries ውስጥ ደግሞ የአርትዖት ሥራ ዳይሬክተር እና የeJournal አርታዒ በመሆን ያገለግላል።

ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 146

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም

አድራሻ

ጉርድ ሾላ፣ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ሜርሲ ፕላዛ 13ኛ ፎቅ ላይ ማግኘት ይቻላል።