ሳኦልም ጊብዓ ወዳለው ቤቱ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ልባቸውን የነካው ኀያላን ሰዎች አብረውት ሄዱ። (1ኛ ሳሙኤል 10፥26)
እስቲ በዚህ ክፍል ላይ እየተባለ ያለውን ነገር አስቡት። እግዚአብሔር ነካቸው። ሚስት እና ልጅ ሳይሆን፣ ወላጅ ወይም አማካሪ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ራሱ። እግዚአብሔር ነካቸው።
በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ወሰን የለሽ ኃይል ያለው እርሱ ነካቸው። ወሰን የለሽ ሥልጣን፣ ወሰን የለሽ ጥበብ፣ ወሰን የለሽ ፍቅር፣ ወሰን የለሽ ቸርነት፣ ወሰን የለሽ ንጽህናና ወሰን የለሽ ፍትህ ያለው እርሱ፣ ልባቸውን ነካ።
ጁፒተርን የሚያክል ፕላኔት ቅንጣት የምታክል የአሸዋ ብናኝ እንዴት መንካት ይችላል? ወደ ውስጥ ሠርጾ መግባት ይቅርና?
የእግዚአብሔርን መንካት አስደናቂ ያደረገው የሚነካው እግዚአብሔር መሆኑ ብቻ አይደለም፤ በራሱ መንካት መኖሩም ጭምር ነው። እውነተኛ የሆነ ግንኙነት ነው። ልብን እና እግዚአብሔርን ማካተቱም ያስደንቃል። ደግሞም እውነተኛ ንክኪን የሚያካትት መሆኑ በጣም የሚደንቅ ነው።
ኀያላኑ እግዚአብሔር የተነገራቸው ሰዎች ብቻ አልነበሩም። በመለኮታዊ ተጽዕኖ ዐሳባቸውን የቀየሩ ብቻም አይደሉም። የታዩና የታወቁ ብቻም አልነበሩም። እግዚአብሔር፣ ወሰን በሌለው ትህትናው፣ ልባቸውን ነክቶታል። እግዚአብሔር ያን ያህል ቀርቧቸዋል። ደግሞም አልጠፉም።
ያንን መንካት እወደዋለሁ። ባገኘሁት ቁጥር ደግሞ ይበልጥ እፈልገዋለሁ። ለራሴም፣ ለእናንተም። እግዚአብሔር በክብሩና ለክብሩ እንደገና እንዲነካኝ እጸልያለሁ። ሁላችንንም እንዲነካን እጸልያለሁ።
ኦ የእግዚአብሔር መንካት! ከእሳት ጋር እንኳ ቢመጣ፣ አሜን ይሁን። ከውኃ ጋርም ከመጣ እንደዚያው፣ አሜን ይሁን። በነፋስም የሚመጣ ከሆነ፣ ኦ እግዚአብሔር ሆይ፣ አሜን ይምጣ። በነጎድጓድና በመብረቅም የመጣ እንደሆነ፣ አሜን፣ በፊቱ እንሰግዳለን።
ኦ ጌታ ሆይ ና። የዚህን ያህል ቅረበን። ንካን፣ አረስርሰን፣ ንፈስብን ደግሞም ስበረን። ቀስም ብለህ ቢሆን ና። ብቻ፣ ና። ውስጣችን ድረስ ና። ልባችንን ንካ።