በመርሕ ደረጃ፣ ደቀ መዝሙርነት እንዴት ይሠራል?

መልስ

ደቀ መዝሙርነት የሚሠራባቸው መንገዶች ዋናነት በመማር እና በመምሰል ነው። ደቀ መዝሙርነት በይበልጥ የሚሠራው በፍቅር ነው። አዳዲስ አማኞችን እግዚአብሔርን የመምሰል መንገድ በፍቅር ስናስተምርና በሚመሰገን ሕይወት ስንኖር፣ የእኛን ሕይወትና አካሄድ በመከተል ክርስቶስን በመምሰል ያድጋሉ (1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16ን ተመልከቱ)።

ትምህርት፦ መጽሐፍ ቅዱስ ወላጆችና መጋቢዎች በአደራ የተሰጧቸውን ሰዎች እንዲያስተምሩ ያዛል (ምሳሌ 6፥6ገላትያ 6፥6ኤፌሶን 6፥41ኛ ተሰሎንቄ 4፥81ኛ ጢሞቴዎስ 1፥18 6፥32ኛ ጢሞቴዎስ 2፥254፥2)። አማኞች እርስ በርሳቸው እንዲተናነጹም ያዝዛል (ሮሜ 15፥14)። 

መምሰል፦ በመጀመሪያ ደረጃ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ይመስላሉ፤ በመቀጠልም አንዱ ሌላውን ይመስላል። በማዳመጥና በመምሰል በእግዚአብሔር ጸጋ እናድጋለን።

  • “እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ” (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥1)።
  • “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፤ የኑሯቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው” (ዕብራውያን 13፥7)።
  • “ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋር ይሆናል” (ፊልጵስዩስ 4፥9)።
  • “አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዐላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ” (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥10)።
  • “ወዳጅ ሆይ፤ መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትምሰል” (3ኛ ዮሐንስ 11)።

ፍቅር፦ ሰዎችን እናንተ ባትወዷቸውም እንኳ ሕይወታችሁን ይመስላሉ። ነገር ግን በፍቅር የሚገዛ መሪ ክርስቶስን ምርጥ በሆነ መልኩ ያሳያል፤ ሰዎችን ስትወዷቸው ደግሞ በይበልጥ ይከተሏችኋል። 

ወዳጅነት፦ ደቀ መዝሙርነት በመሠረቱ ወዳጅነት ነው፤ ነገር ግን ወደ ክርስቶስ የሚያተኩር ወዳጅነት ነው። ጓደኞች ምንድን ነው የሚያደርጉት? አንዱ ሌላኛውን ይመስላል። በደቀ መዝሙርነት ክርስቶስን በመምሰል እንድናድግና ክርስቶስን በመምሰል እንዲያድጉ ለመርዳት ከሌሎች ጋር ወዳጅነት እንፈጥራለን።

ደቀ መዝሙር መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

(ሀ) በክርስትና የቆዩ ቅዱሳን እንዴት እንደሚሠሩ፣ እንደሚያርፉ፣ ቤተሰብ እንደሚያሳድጉ፣ አለመግባባቶችን እንደሚፈቱ፣ ወንጌልን ለጎረቤቶቻቸው እንደሚነግሩ፣ መከራን እንደሚታገሡ፣ በቤተ ክርስቲያን እንደሚያገለግሉ እና ኀጢአትን እንደሚዋጉ የሚያካትቱትን ሁሉ ነገሮች አድምጡ፤ ደግሞም ተመልከቱ።

(ለ) እነርሱን ምሰሉ።