በቀብር ሥነ ሥርዐት  ላይ ወንጌልን እንዴት እንስበክ?

“ወደ ገነት እየጠቆምክ አትስበካቸው፤ አልያም ወደ ሲኦል። ነገር ግን ለታዳሚዎቹ ወንጌሉን ብቻ ስበክ።” ይህ በማላውቀው ሰው የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ስለመስበክ ያገኘሁት ጠቃሚ ምክር ነው። የቀብር ሥነ ሥርዐታችን ምንም ዐይነት ቢሆን፣ ይህ ለተግባራችን ወሳኝ መርህ ነው። በቀብር ሥነ ሥርዐቶቻችን ላይ ትኩረታችን የሟቹን ሕይወት ማክበርና ማስታወስ ቢሆንም፣ በዋነኛነት ግን ሥነ ሥርዐቱ ለታደሙት ሊሆን ይገባል።

Continue Readingበቀብር ሥነ ሥርዐት  ላይ ወንጌልን እንዴት እንስበክ?
ወንጌል ስብከትን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ማቆራኘት

የወንጌል ስብከትንና ቤተክርስቲያንን የሚያገናኝ ትልቅ ምስል አለ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የመጀመሪያ ምዕራፎች ያስተዋለን ከሆነ፣ ሐዋሪያቱ ትንሣኤውን ሲሰብኩ ከጀርባ ደግሞ በጋራ የሚኖሩ፣ ያላቸውን በአንድነት ያደረጉና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰዎች መሃከል በሞገስ የሚመላለሱ ሰዎች ያሉባት ቤተክርስቲያን ነበረች (2፥47፤ 5፥13)። በሆነ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ከወንጌል ስብከት ጀርባ እንደ ምስክር ሆኖ ያገለግላል። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ቅዱሳንን በሞገስ እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል፤ ብዙዎችንም ወደ ድነት የመራ ይመስላል።

Continue Readingወንጌል ስብከትን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ማቆራኘት
በዘመናችን ያለው የአብዛኛው ስብከት ችግር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት እንደ መፍትሔ

አብዛኛውን ጊዜ ስብከቶች የሚያተኩሩት፣ የተሳካ ትዳር ለመመሥረት ወይም በባሕላችን ልጆችን ማሳደግ የሚቻልበት መንገድ ላይ ነው። በርግጥ በቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ስብከቶች ተስማሚ እና አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሁለት ችግሮች ይከሰታሉ። በመጀመሪያ፣ ቅዱሳን ጽሑፎች ስለ እነዚህ ጉዳዮች የሚናገሩት ነገር በአብዛኛው ችላ ይባላል። ምን ያህሎቹ ስብከቶች ጳውሎስ ስለ ወንዶች እና ሴቶች ሚና ምን እንደሚል በታማኝነት እና በአስፈላጊ ጊዜ ይናገራሉ (ኤፌሶን 5፥22-33)? ወይስ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚናገሩት እናፍራለን? ሁለተኛ፣ እና ምናልባትም ከዚ በከፋ ሁኔታ፣ እንደዚህ ዐይነት ስብከቶች የሚሰበኩት (ሁልጊዜም ማለት ይቻላል) በአግድመት ደረጃ (horizontal level) ነው።

Continue Readingበዘመናችን ያለው የአብዛኛው ስብከት ችግር እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገረ መለኮት እንደ መፍትሔ
ወንጌል መስበክ ምን ማለት ነው?

ወንጌል መስበክ ማለት ክርስቶስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ያደረገውን መልካም ዜና መናገር ነው። ይህንም ለማድረግ እነዚህን እውነቶች የግድ መናገር ይኖርብናል፦ 1. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው (1 ዮሐንስ 1፥5)። እርሱ የሚታይውም የማይታየውም ዓለም ፈጣሪ…

Continue Readingወንጌል መስበክ ምን ማለት ነው?
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማለት ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም በመደበኛነት ተሰባስበው፣ በወንጌል ስብከትና በወንጌል በተደነገጉ ሥርዐቶች በኢየሱስ ክርስቶስና በመንግሥቱ ያላቸውን ኅብረት በይፋ የሚያጸኑበትና እርስ በርስ የሚተያዩበት ስብስብ ነው። ይህ ትርጉም የተንዛዛ እንደ…

Continue Readingአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?
ወንጌል ምንድን ነው?

ወንጌል ምንድን ነው? በወንጌላውያን አማንያን ዘንድ ለረጅም ጊዜ እየተካሄዱ ካሉ ክርክሮች መካከል ዋነኛው “ወንጌልን በምን መልኩ እንረዳው?” የሚል ነው። የወንጌል ትርጉሙስ ምንድን ነው? አንዳንዶች እንደሚረዱት፣ “ወንጌል ማለት ኅጢአተኛ የሆኑ ሰዎች…

Continue Readingወንጌል ምንድን ነው?