ወንጌል ስብከትን በተመለከተ ያሉ መጥፎ ልማዶች

ወንጌል መስበክ ማለት የምሥራቹን ቃል መናገር ማለት ነው፤ ስለዚህ ትልቁ ጥፋት የሚሆነው ከነጭራሹ አለመናገር ነው። አንዳንድ ግዜ ማኅበራዊ ሥራ የሚሠሩ ክርስቲያኖች፣ ሰዎችን በመርዳትና በመንከባከብ ወንጌል የሰበኩ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ሳንናገር ወንጌል ስብከት የለም።

0 Comments
ወንጌልን በቀብር ሥነ ሥርዐት  ላይ መስበክ

“ወደ ገነት እየጠቆምክ አትስበካቸው፤ አልያም ወደ ሲኦል። ነገር ግን ለታዳሚዎቹ ወንጌሉን ብቻ ስበክ።” ይህ በማላውቀው ሰው የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ስለመስበክ ያገኘሁት ጠቃሚ ምክር ነው። የቀብር ሥነ ሥርዐታችን ምንም ዐይነት ቢሆን፣ ይህ ለተግባራችን ወሳኝ መርህ ነው። በቀብር ሥነ ሥርዐቶቻችን ላይ ትኩረታችን የሟቹን ሕይወት ማክበርና ማስታወስ ቢሆንም፣ በዋነኛነት ግን ሥነ ሥርዐቱ ለታደሙት ሊሆን ይገባል።

0 Comments
ወንጌል ስብከትን ከቤተ ክርስቲያን ማቆራኘት

የወንጌል ስብከትንና ቤተክርስቲያንን የሚያገናኝ ትልቅ ምስል አለ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የመጀመሪያ ምዕራፎች ያስተዋለን ከሆነ፣ ሐዋሪያቱ ትንሣኤውን ሲሰብኩ ከጀርባ ደግሞ በጋራ የሚኖሩ፣ ያላቸውን በአንድነት ያደረጉና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰዎች መሃከል በሞገስ የሚመላለሱ ሰዎች ያሉባት ቤተክርስቲያን ነበረች (2፥47፤ 5፥13)። በሆነ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ከወንጌል ስብከት ጀርባ እንደ ምስክር ሆኖ ያገለግላል። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ቅዱሳንን በሞገስ እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል፤ ብዙዎችንም ወደ ድነት የመራ ይመስላል።

0 Comments
የመንፈሳዊ ኮንፍረንሶች ችግር

ለምንኖርበት ማኅበረሰብ ወንጌልን መስበክ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ክርስቲያኖችን ለማሳመን ብዙም ጥረት አያስፈልግም። እንዲያውም አንድ የመንፈሳዊ ኮንፍረንስ ሥራ ላይ ተሳታፊ ሰዎችን ማግኘት ከባድ ነገር አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ጊዜ ወንጌልን ለማኅበረሰባችን…

0 Comments
ወንጌል መስበክ ምን ማለት ነው?

ወንጌል መስበክ ማለት ክርስቶስ ኅጢአተኞችን ለማዳን ያደረገውን መልካም ዜና መናገር ነው። ይህንንም ለማድረግ እነዚህን እውነቶች የግድ መናገር ይኖርብናል፦ 1. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 1፥5)። እርሱ የሚታይውም የማይታየውም ዓለም ፈጣሪ…

0 Comments