ወደ ድንቅ የእግዚአብሔር ምስጢር ተራሮች ገስግሱ

የእግዚአብሔርን የአሠራር መንገዶች ለማወቅ ያለንን ቸልተኝነትን በመቃረን፣ እርሱን ለማድነቅና ለማምለክ የእግዚአብሔርን መንገድ እንደ መሠረት በመጠቀም የሚናገሩ የተለያዩ ጽሑፎችን አንብቤአለሁ። እንዲሁም የተለያዩ ሰባኪዎች በየምስባካቸው በዚህ መንገድ ሲሰብኩ ሰምቻለሁ። ይህንንም ለማድረግ የሚጠቀሙት ቃል “ምስጢር ” የሚለውን አዎንታዊ ቃል ሲሆን በዚህም የእግዚአብሔርን ክቡርነትና ልዕልና ምን ያህል እንደማናውቅ ተረድተን መደነቅ እንዳለብን ይነግሩናል።

0 Comments
ክቡር የሆነው የክርስቶስ ደም ኀይል

በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ የሚመሩ ደግሞ በቃል ከመቀበል ባለፈ በውስጣቸው አስተውሎትና እርግጠኝነት አላቸው። አንተ ግን ቆም ብለህ እንዴት እንደሆነ ጠይቀህ ታውቃለህ? ደሙ እንደ ምትሃት ነው የሚሠራው? በርግጥ በደሙ ውስጥ ኃይል ካለ፤ ይህንን እውነት እንዴት ነው መረዳት የሚቻለው? "ድንቅ ሥራን የሚሠራ ኃይል" በማለት ስናበሥር የሚገለጠው እውነት ምን ይሆን?

0 Comments
በእምነት ያልተደረገ ሁሉ ኅጢአት ነውን?

በዮሐንስ አፈወርቅ (347-407 ዓ.ም.) ዘመን የነበሩ ሰዎች፣ በሮሜ 14፥23 “በእምነት ያልተደረገ ሁሉ ኅጢአት ነውና” የሚለውን የጳውሎስን ቃላት ትርጉም ለመገደብ ሞክረዋል። ዮሐንስ አፈወርቅ ራሱም እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “በዚህ ክፍል ጳውሎስ ለመናገር…

0 Comments
ቅድመ ሁኔታ የሌለው ምርጫን ለመቀበል አምስት ምክንያቶች

'ያለ ቅድመ ሁኔታ ምርጫ' ላይ ያቀረብኩት ተቃውሞ ሁሉ ውድቅ የሆነው፣ ሮሜ 9ን ማብራራት ሲያቅተኝ ነው።. ምዕራፉ የሚጀምረው ጳውሎስ ለ አይሁድ ወገኖቹ ሲል የተረገመ እና ከክርስቶስም ተለይቶ የተጣለ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት በማሳየት ነው (ሮሜ 9፥3)። ይህ የሚያሳየው አንዳንድ አይሁዶች እየጠፉ እንደሆነ ነው። ይህም እግዚአብሔር ለአይሁዶች የገባውን የተስፋ ቃል ላይ ጥያቄ ያስነሣል። አልተሳካም ነበር? ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቃል ተሽሮአል ማለት አይደለም” ሲል ይመልሳል (ሮሜ 9፥6)። ለምን አይሆንም?

0 Comments
የመከራ አምስት ዓላማዎች | ታሕሳስ 30

እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን። (ሮሜ 8፥28) የመከራችንን ጥቃቅን ምክንያቶች አስረግጠን ባናውቃቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እምነትን የሚያጸኑ ጉልህ ምክንያቶችን ይሰጠናል። እነዚህንም የምናስታውስበት መንገድ…

0 Comments