እምነት ምንድን ነው?

አር. ሲ. ስፕሮል

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች፣ “ብቻ ትንሽ እምነት ይኑርህ” ሲሉ እንሰማለን። እምነት ግን ምንድነው? ወደ ማይታወቅ ጨለማ በጭፍን የሚደረግ ጉዞ ነውን? አንድን ነገር ያለ ማስረጃ ማመን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እምነት የሚሰጠው ፍቺ ምንድነው?

በዚህ አጭር መጽሐፍ ውስጥ ዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮል ስለ እምነት የመጽሐፍ ቅዱስን ፍቺ ለማግኘት ዕብራውያን 11ን በሚገባ ይመለከታሉ። ይህም እምነት እግዚአብሔርን ማመንና በቃሉ መሠረት መኖር እንደሆነ ጠቁመዋል። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ታሪክ በመቃኘት፣ ወደ ፊት ሊሆን ያለውን ሳያውቁ እንዴት በእግዚአብሔር እንደታመኑ ያሳዩናል። እንደ እነርሱ ሁሉ እኛም በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ስንጋፈጥ እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ይኖርብናል።

በዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮል የተዘጋጀው የወሳኝ ጥያቄዎች መድብል፣ ብዙ ክርስቲያኖች ለሚጠይቋቸው መሠረታዊ ጥያቄዎችና ለተጠራጣሪ ሰዎች ሙግት አጥጋቢ መልስ የሚሰጡ ናቸው። 

ስለ ጸሐፊው

ዶ/ር አር. ሲ. ስፕሮል የሊጎኔር ሚንስትሪ መሥራች፣ በሳንፎርድ ፍሎሪዳ የቅዱስ እንድርያስ ቤተ ክርስቲያን መሥራች መጋቢ፣ የሪፎርሜሽን ባይብል ኮሌጅ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንትና ሥራ አስኪያጅ ነበሩ። “The Holiness of God” የሚለውን መጽሐፍ ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ መጽሐፍት ደራሲ ነበሩ።

ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 78

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም