መልስ
መጽሐፍ ቅዱስ ሊካድ በማይቻል ግልጽነት በርካታ ነጥቦችን ያስተምራል።
- የተልእኮዎች ውጤት ከእግዚአብሔር እንጂ መሣሪያ ከሆነው ከሰው አይደሉም። ”እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም።” (1ኛ ቆሮንቶስ 3፥6-7)።
- የእኛ ድርሻ ወንጌልን በታማኝነት ማወጅ እና ለውጤቱ በእግዚአብሔር መታመን ነው። ”አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ። ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና” (የሐዋርያት ሥራ 20፥25-27)።
- ስለዚህ በተልዕኮዎች ውስጥ እውነተኛ ስኬት የሚለካው ለተግባሩ ባለን ታማኝነት እንጂ ወዲያውኑ በሚታዩ ውጤቶች አይደለም። “እንግዲህ ሰው ሁሉ እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምስጢር ባለ ዐደራዎች ሊቈጥረን ይገባል። ባለ ዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው” (1ኛ ቆሮንቶስ 4፥1-2)።
- የክርስቲያን ተልእኮዎች መሠረታዊ ተፈጥሮ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው። “የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፥7)። ውጤቱን ለመለካት የሚደረገው ሙከራ ብዙውን ጊዜ በእይታ ለመኖር የሚደረግ ሙከራ ነው። ስኬትን እንደ “ታማኝነት” መግለጽ ለማቀፍ ከባድ ነው፤ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ መታመንን ይጠይቃል።