ወንጌል ምንድን ነው?

በ ግሬግ ጊልበርት

 ይሄ መጽሐፍ አዲስ መሠረት ለመጣል የሚታትር አይደለም፤ ይልቅ የተዘነጋውን የቀድሞ መሠረት እንደ አዲስ ይዳስሳል። የግሬግ አስተሳሰብ እና የሐሳቡ ፍሰት በጣም የሚያስደንቅ ነው። ይሄ መጽሐፍ ጥቂት የበሰሉ ክርስቲያኖችን አስተሳሰብ ብቻ የሚቀርጽ አይደለም። ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ለወጣት ክርስቲያኖች፣ ክርስቶስን ላላመኑ ጭምር ወንጌል ምን እንደሆነ በግልጽ የሚያብራራ መጽሐፍ ነው። አንብቡት! ለሌሎችም በልግስና ማከፋፈል እንድትችሉ በርከት አድርጋችሁ ግዙት።

ስለ ጸሐፊው

ግሬግ ጊልበርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዬል ዩኒቨርስቲ ያገኘ ሲሆን፣ ማስተርስ ኦፍ ዲቪኒቲ ደግሞ ከሳውዘርን ባፕቲስት ሥነ መለኮት ትምህርት ቤት ወስዷል። አሁን ላይ በሉዊቪል ኬንታኪ ከተማ ያለች ሰርድ አቬኒዩ ባፕቲስት በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋና መጋቢ ነው።

አስተያየት
“እውነተኛ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የወንጌል ማብራሪያ ይሰጣል። ደግሞም ክርስቲያኖች ከክብሩ ወንጌል የጎደለ መልእክትን እንዲለዩ ያስታጥቃል። መሻቴ ይህ መጽሐፍ እያንዳንዱ መጋቢና የቤተ ክርስቲያን አባል እጅ እንዲገባ ነው።”
ሲ.ጄ ማሃነይ፤ ሶቨሬን ግሬስ ሚኒስትሪስ
—————————-
“ይህች ስለ ወንጌል የምታወራ ትንሽ መጽሐፍ፣ በቅርብ ዓመታት ካነበብኳቸው መጽሐፎች ሁሉ ግልጽና አስፈላጊ መጽሐፍ ነች።”
ማርክ ዴቨር፤ ዋና መጋቢ፣ ካፒቶል ሂል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን፣ ዋሽንግተን ዲሲ 
—————————-
“ግሬግ ጊልበርት የዛሬዋን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል ከተጠሩ ብሩህ እና እጅግ ታማኝ ወንድሞች መካከል አንዱ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት በሙላት፣ በታማኝነት፣ እና ልብ ዘልቆ በሚገባ መንገድ ያቀርብልናል።”
አልበርት ሞህለር፤ ፕሬዚደንት፣ ሳውዘርን ባፕቲስት ሥነ መለኮት ሴሚናሪ
—————————-
“ወንጌል ምንድን ነው? የሚለው መጽሐፍ ቀልባችሁን ይገዛል፤ ደግሞም በጸጋው በወንጌል ለእርሱ ክብር ላዳናችሁ ለእግዚአብሔር ልባችሁን በፍቅር ያቀልጣል።”
ዴቪድ ፕላት፤ ዋና መጋቢ፣ ዘ ቸርች አት ብሩክሂልስ፣ በርሚንግሃም፣ አላባማ
ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 124 

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም