ጤናማ ቤተ ክርስቲያን ምንድን ነው?

ማርክ ዴቨር

ማርክ ዴቨር የጤናማ ቤተ ክርስቲያን ቁልፍ መገለጫዎች፦ ገላጭ ስብከት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ መለኮት፣ እና የወንጌል ትክክለኛ መረዳት ምን እንደሆነ አማኞች መለየት እንዲችሉ ይጥራል። በመቀጠልም እነዚህን መገለጫዎች በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን እንድናሳድግ ይጣራል። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን ፈለግ በመከተል እና ከመጋቢዎች አንሥቶ እስከ ምዕመኑ ያሉትን አባላት ሁሉ በማማከል፣ ሁሉም አማኞች በየፊናቸው የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ይሞግታል። ይሄ መጽሐፍ እያንዳንዳችን በክርስቶስ አካል ውስጥ እግዚአብሔር የሰጠንን ድርሻ እንድንወጣ ጊዜ የማይሽረው እውነት እና ተግባራዊ መርህ ያቀርባል።

ስለ ጸሐፊው

ማርክ ዴቨር (PhD, University of Cambridge) የ”What Does God Want of Us Anyway?” እና የሌሎች በርካታ መጽሐፍት ደራሲ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲ በምትገኘው በካፒቶል ሂል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዋና መጋቢነት ያገለግላል፤ ከመጋቢነት ኅላፊነቱ ባሻገር የ9Marks ፕሬዚዳንት ነው።

ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 128

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም

አድራሻ

ጉርድ ሾላ፣ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ሜርሲ ፕላዛ 13ኛ ፎቅ ላይ ማግኘት ይቻላል።