“እውነተኛ የቤተ ክርስትያን አባልነት” ምንድን ነው?

መልስ

“እውነተኛ የቤተ ክርስትያን አባልነት” እነዚህን አራት ነገሮች ማለት ነው፦

  1. የቤተ ክርስቲያን አባላት ክርስቲያኖች መሆን አለባቸው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ፣ ወደ ቤተ ክርስትያን ይጨመሩ የነበሩት በወንጌሉ ያመኑት ነበሩ (2፥4147)። ጳውሎስ ለአብያተ ክርስቲያናት የጻፋቸው ደብዳቤዎች ለክርስቲያኖች የተጻፉ ደብዳቤዎች ናቸው (ሮሜ 1፥71 ቆሮንቶስ 1፥2)። ምንም እንኳ የትኛዋም ቤተ ክርስቲያን ፍጹም በሆነ መልኩ ክርስቲያን የሆነውን እና ያልሆነውን መለየት ባትችልም፣ እያንዳንዷ ቤተ ክርስቲያን ግን አባልነትን መስጠት ያለባት በተዓማኒነት በክርስቶስ ያላቸውን እምነት በግልጥ ለሚያውጁ ሰዎች ብቻ ነው።
  2. የቤተ ክርስቲያን አባላት ቋሚ ተካፋዮች መሆን አለባቸው። የቤተ ክርስቲያን አባልነት፣ አብያተ ክርስቲያናት የአባላቶቻቸውን ሕይወት እንዲከታተሉ ይረዳቸዋል። አንድ ሰው በቋሚነት የማይካፈል ከሆነ ግን፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ የዚያን ሰው ሕይወት የምታውቅበት ምንም መንገድ አይኖራትም።
  3. አባላት ቤተ ክርስቲያንን አንደ ዋነኛ የኅብረት እና የአገልግሎት ቦታቸው ማየት አለባቸው። “የመካነ ኢየሱስ አባል ነኝ፤ ነገር ግን ዋና አገልግሎቴ…” — ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ዓረፍተ ነገር አጀማመር ነው። የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባላት በተጻፉ ብዙ “እርስ በርሳችሁ” የተሞሉ መጽሐፍት ናቸው። ይህ ማለት፣ ክርስቲያኖች በአንዳንድ አጋጣሚዎች ከሌላ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች ጋር ሲገናኙ እነዚያን ትእዛዛት መፈጸም የለባቸውም ማለት አይደለም። ቢሆንም ግን፣ የአዲስ ኪዳን ዋና ዓላማ፣ ክርስቲያኖች እነዚያን ትእዛዛት፣ በዋነኛነት ተጠያቂ በሚሆኑለት አንድ ጽኑ ቡድን መካከል እንዲፈጽሙት ነው (ለምሳሌ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 12)።
  4. የቤተ ክርስትያን አባላት ግልጽ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መብቶች እና ኀላፊነቶች ሊኖሯቸው ይገባል። የአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባላት የጌታ ራትን የመውሰድ መብት ሊኖራቸው ይገባል። በተጨማሪም እነዚህ ኀላፊነቶች ይኖሯቸዋል፦
  1. ለቤተ ክርስቲያን መጸለይ።
  2. ከሌሎች የቤተ ክርስቲያን አባላት ጋር፣ ስለ ሌላው ግድ የሚሰኙበት፣ የሚበረታቱበት፣ እና እርስ በርሳቸውም የሚማማሩበት፣ ግልጽነት የተሞላበት ግንኙነት ውስጥ መሆን (ኤፌሶን 4፥15-16)።
  3. ለቤተ ክርስቲያን አመራር እና ትምህርት መገዛት (ዕብራውያን 13፥17)።
  4. በአካል ውስጥ ያለውን አንድነት ማጠናከር (ኤፌሶን 4፥3)።
  5. የቤተ ክርስቲያኒቷን አገልግሎት በገንዘብ መደገፍ(ገላቲያ 6፥6)።
  6. የጸጋ ስጦታዎቻቸውን በመጠቀም በቻሉት ሁሉ የክርስቶስን አካል መገንባት (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7)።