ኢየሱስ ማን ነው?

በ ግሬግ ጊልበርት

አንድ ታዋቂ የታሪክ ተመራማሪ እንደተናገረው፣ በግላችሁ ስለ እርሱ የትኛውም ዐይነት አመለካከት ቢኖራችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በምዕራባውያን የስልጣኔ ታሪክ ውስጥ ማዕከላዊ ግለሰብ ነው። አንዳንዶች በዐመፅ ሲገፋት፣ ሌሎች ደግሞ በመሰጠት አምልከውታል። ብዙ ሰዎች ግን አሁንም ድረስ በርግጥ እርሱ ማን እንደነበር፣ ለምን እንደመጣ፣ ወይም ስለ ራሱ የተናገራቸውን ነገሮች አያውቁም። ኢየሱስ ማነው? የሚለው መጽሐፍ ስለ ኢየሱስ ሕይወት፣ ስለ ተናገራቸው ነገሮች፣ እና መከራ ስለ መቀበሉ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ይሰጠናል። ይሄ መጽሐፍ ክርስቲያን ላልሆኑ እና ለአዲስ ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ ማን እንደሆነ አሳማኝ ሙግት ያቀርባል። በመጨረሻም አንባቢዎች በዓለም ላይ የኖረውን ምርጥ ሰው አስደናቂ ትምህርቶችና ታሪክ ለዋጭ አካሄዱን በጥንቃቄ እንዲገነዘቡ ያበረታታል።

ስለ ጸሐፊው

ግሬግ ጊልበርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ከዬል ዩኒቨርስቲ ያገኘ ሲሆን፣ ማስተርስ ኦፍ ዲቪኒቲ ደግሞ ከሳውዘርን ባፕቲስት ሥነ መለኮት ትምህርት ቤት ወስዷል። አሁን ላይ በሉዊቪል ኬንታኪ ከተማ ያለች ሰርድ አቬኒዩ ባፕቲስት በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዋና መጋቢ ነው።

አስተያየት
“ጊልበርት ተነባቢ እና ቅልብጭ ባለ አቀራረብ፣ ክርስቶስ ስለ ራሱ የተናገራቸውን እውነታዎች ለማሳየት የቅዱሳት መጽሐፍትን ገጾች ያገላብጣል።”
ጂም ዳሊይ፤ ፕሬዝዳንት፣ ፎከስ ኦን ዘ ፋምሊ
—————————-
“ይሄ መጽሐፍ በዓለም ከኖሩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አስደናቂውን ሰው የሚያስተዋውቅ ትልቅ ግብዓት ነው።”
አሰልጣኝ ሮን ብራውን፤ ኔብራስካ ኮርንሀስከርስ ዩንቨርስቲ
—————————-
“ጊልበርት ታዋቂ በሆኑት ክስተቶች ላይ አዲስ ብርሃን ይፈነጥቃል፤ እውነታዎችን ከአስፈላጊነታቸው ጋር ያዛምዳል። ይህ ኢየሱስን እንድታውቁ ለእናንተ ለአንባቢዎች የቀረበ ግብዣ ነው።”
ማርክ ዴቨር፤ ዋና መጋቢ፣ ካፒቶል ሂል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን፣ ዋሽንግተን፣ ዲሲ፤ ፕሬዝዳንት፣ 9ማርክስ
 
—————————-
“የግሬግ ትልቁ ሀብት መሠረታዊ ነገሮችን በቀላል አነጋገር የመግለጽ ችሎታው ነው። ኢየሱስ ማነው? የሚለው መጽሐፍ ክርስቶስ ራሱን ያቀረበበትን መንገድ፣ እኛ እርሱን ዳግም ካበጀንበት ምስል እንዴት መለየት እንደምንችል ይረዳናል።”
ጄ.ዲ.ግሪር፤ ዋና መጋቢ፣ ዘ ሰሚት ቤተ ክርስቲያን፣ ዱርሃም፣ ኖርዝ ካሮሊና 
ስለ መጽሐፉ

አሳታሚ፦ ወንጌሉ ሚኒስትሪስ

የገጽ ብዛት፦ 154

የታተመበት ጊዜ (ትርጉም)፦ 2015 ዓ.ም