ለምንድን ነው ሁሉም ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን መቀላቀል ያለበት?

መልስ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያዝ ሁሉም ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን መቀላቀል አለበት። ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሁሉም ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንን መቀላቀል አለበት” የሚል ቀጥተኛ ትእዛዝ ባይገኝም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ነገሮች ግን ሁሉም ክርስቲያን የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል መሆን እንዳለበት ይጠቁማሉ።

  1. ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተው በእርሱ የሚያምኑትን የሚለይ፣ የሚያጸና እና የሚያስተዳድር ግልፅ የሆነ ምድራዊ ተቋም እንዲሆን ነው (ማቴዎስ 16፥18-1918፥15-20)። ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተው ለዓለም ስለ ራሱ ያለውን መልካም ዜና ለማሳየት የእርሱ የሆኑትን ግልጽ ያደርግ ዘንድ ነው (ዮሐንስ 17፥2123ኤፌሶን 3፥10)። ኢየሱስ የእርሱ የሆኑትን እና የእርሱ ያልሆኑትን ዓለም ለይቶ እንዲያውቅ ይፈልጋል። እና ዓለም የእርሱ የሆኑትን እና የእርሱ ያልሆኑትን በምንድን ነው ለይቶ ማወቅ የሚችለው? የትኞቹ ሰዎች በተገለጠ ሁኔታ ለዚህ ዓላማ ብሎ ባቋቋመው (በግልጽ በሚታይ ተቋም ውስጥ ካሉት) የእርሱ ከሆኑት ጋር ራሳቸውን አንድ እንደሚያደርጉ በማየት ነው። የቤተ ክርስቲያኑ አባላት የሆኑትን በማየት ነው። አንዳንድ ሰዎች የምንም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባል ሳይሆኑ የዓለም አቀፋይቱ ቤተ ክርስቲያን አካል ነኝ ቢሉ፣ ኢየሱስ ለእነርሱ እና ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ዓላማ እየካዱ ነው። ኢየሱስ የእርሱ የሆኑ ሰዎች፣ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አብረው ኅብረት በማድረግ በሚታይ እና ግልፅ በሆነ መልኩ ተለይተው እንዲታወቁ ይፈልጋል።
  2. መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ክርስቲያኖች ለመሪዎቻቸው እንዲገዙ ያዛል (ዕብራውያን 13፥171ኛ ተሰሎንቄ 5፥12-13)። ይሄንን ማድረግ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ በግልፅ መንጋዎቻቸውን በመቀላቀል እና ከዚያም የተነሣ “የምታስተምሩትን እሰማለሁ፤ የምታሳዩትን አቅጣጫ እከተላለሁ፤ ደግሞም ለአመራራችሁ እገዛለሁ” በማለት ነው። አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን በመቀላቀል ለመሪዎች ሳይገዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን “ለመሪዎች ተገዙ” የሚለውን ትእዛዝ መታዘዝ የሚቻልበት ሌላ መንገድ የለም።