- መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ያቋቋመው ኢየሱስ ሲሆን፣ ሁሉም ሐዋሪያት አገልግሎታቸዉን ያካሄዱት በእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በኩል ነው። በአዲስ ኪዳን የአንድ ክርስቲያን ሕይወት፣ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ማለት ነው። በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖችም ይህንኑ መጠበቅ እና መናፈቅ አለባቸው።
- ቤተ ክርስቲያን ማለት አባላቶቿ ናቸዉ። በአዲስ ኪዳን “ቤተ ክርስቲያን“ መሆን ማለት፣ ከአባላቶቿ አንዱ መሆን ማለት ነዉ (የሐዋሪያት ሥራን አንብቡ)። ኢየሱስ ሊያድናት እና ከራሱ ጋር ሊያስታርቃት የመጣው ቤተ ክርስቲያንን ስለሆነ፣ የዚያ አካል መሆን ያስፈልጋል።
- የጌታ እራት ለመዉሰድ ቅድመ ሁኔታ ነው። የጌታ እራት ለተሰበሰበ ቤተ ክርስትያን ማለትም ለአባላቶቿ የሚሆን ማዕድ ነዉ (1ኛ ቆሮንቶስ 11፥20፣ 33)። የጌታን ራት ደግሞ መዉሰድ ያስፈልጋል። የቤተ ክርስቲያንን ቡድን ለሕዝቦች የሚያሳይ “ማሊያ” ነው።
- ኢየሱስን በይፋ መወከል የሚቻልበት ነው። አባልነት ማለት በሕዝቦች መካከል የክርስቶስ መንግሥት ዜጋ እና የአባልነት መታወቂያ ያለን የኢየሱስ ተወካዮች መሆናችንን፣ ቤተ ክርስቲያን የምታረጋግጥበት ነዉ። ኢየሱስን ደግሞ በይፋ መወከል ያስፈልጋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ …
- የላቀ ውግንናችን የሚታወጅበት ነው። “ማልያ” መልበስ የአንድ ቡድን አባል መሆናችንን በግልጽ እንደሚያሳየው ሁሉ፣ የቤተ ክርስቲያን አባልነት የላቀ ውግንናችን ከኢየሱስ ጋር መሆኑን የሚያሳይ የአደባባይ ምስክርነት ነዉ። መከራ እና ስደት ሊመጣ ይችላል፤ ሆኖም ግን ከአንደበታችን የሚወጣው ብቸኛ ቃል “ከኢየሱስ ጋር ነኝ” የሚል ይሆናል።
- መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎችን የምንላበስበት እና የምንለማመድበት ነው። ክርስቲያኖች “የክርስቶስ አካል”፣ “የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ”፣ “የእግዚአብሔር ቤተሰብ” እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘይቤያዊ አነጋገሮችን መኖር እና መላበስ የሚችሉት፣ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተጠያቂነት መዋቅር ዉስጥ ነዉ (1ኛ ቆሮንቶስ 12)። የአካሉን መያያዝ፣ የመቅደሱን መንፈሳዊ ሙላት፣ እና በቤተሰቡ መሃል ሊኖር የሚችለዉን ደኅንነትና ቅርብ ግንኙነት መለማመድ ያስፈልጋል።
- ሌሎች ክርስቲያኖችን የምናገለግልበት መንገድ ነው። አባልነት በምድር ላይ ለየትኞቹ ክርስቲያኖች የመዉደድ፣ የማገለገል፣ የማስጠንቀቅ እና የማበረታታት ኅላፊነት እንዳለብን እንድናዉቅ ይረዳናል። ለክርስቶስ አካል ያለብንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኅላፊነት እንድንወጣ ያስችለናል (ለምሳሌ ኤፌሶን 4፥11-16፣ 25-32)።
- ክርስቲያን መሪዎችን የምንከተልበት መንገድ ነዉ። አባልነት በምድር ላይ የትኞቹን ክርስቲያን መሪዎች መታዘዝ እና መከተል እንዳለብን እንድናዉቅ ይረዳናል። እናም ለእነርሱ ያለብንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኅላፊነት እንድንወጣ ይረዳናል (ዕብራዉያን 13፥7፣ 17)።
- ክርስቲያን መሪዎች መምራት እንዲችሉ ያግዛቸዋል። አባልነት ክርስቲያን መሪዎች በምድር ላይ ላሉ ለየትኞቹ ክርስቲያኖች “እንደሚጠየቁ” እንዲያውቁ ያደረጋቸዋል (የሐዋሪያት ሥራ 20፥28፣ 1ኛ ጴጥሮስ 5፥2)።
- ቤተ ከርስቲያናዊ ተግሳጽን[1] ለመለማመድ ያስችላል። ቤተ ከርስቲያናዊ ተግሳጽን በኅላፊነት፣ በጥበብ እና በፍቅር ማካሄድ የሚቻልበትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስፍራ ይሰጠናል (1ኛ ቆሮንቶስ 5)።
- ለክርስቲያናዊ ሕይወት ቅርጽ ይሰጣል። ክርስቶስን “መታዘዝ” እና “መከተል” እፈልጋለሁ የሚል ክርስቲያን በተጨባጭ ሁኔታ፣ በሥልጣን ሥር እውነታውን እንዲለማመድ ያስችለዋል (ዮሐንስ ወንጌል 14፥15፣ 1ኛ ዮሐንስ 2፥19፣ 4፥20-21)።
- ተመልካቾችን ያበዛል እና ሕዝቦችን ይጋብዛል። አባልነት፣ የክርስቶስን ሌላኛውን አገዛዝ መላው ዓለም እንዲመለከተው ለእይታ ያስቀምጣል (ማቴዎስ ወንጌል 5፥13፣ ዮሐንስ ወንጌል 13፥34-35፣ ኤፌሶን 3፥10፣ 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9-12)። በቤተ ክርስቲያን አባልነት ዙሪያ የተሰመረዉ ወሰን፣ ሰዎችን ወደ ተሻለ ነገር የሚጋብዝ ማኅበረሰብ ይፈጥራል።
ጆናታን ሊማን
ከዚህ በላይ ያለዉ ምንባብ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት፦ ዓለም ኢየሱስን ማን እንደሚወክል የሚያውቅበት የሚልበቅርቡ ከሚወጣ የጆናታን ሊማን መጽሐፍ የተወሰደ ነው፤ ከክሮስዌይ፣ 2012 እ.ኤ.አ ነዉ።
[1] በተለምዶ “የጥሞና ጊዜ” የሚባለው ማለት ነው።