ወንጌል ስብከትን በተመለከተ ያሉ መጥፎ ልማዶች

ወንጌል መስበክ ማለት የምሥራቹን ቃል መናገር ማለት ነው፤ ስለዚህ ትልቁ ጥፋት የሚሆነው ከነጭራሹ አለመናገር ነው። አንዳንድ ግዜ ማኅበራዊ ሥራ የሚሠሩ ክርስቲያኖች፣ ሰዎችን በመርዳትና በመንከባከብ ወንጌል የሰበኩ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ሳንናገር ወንጌል ስብከት የለም።

Continue Readingወንጌል ስብከትን በተመለከተ ያሉ መጥፎ ልማዶች
ወንጌል ስብከትን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ማቆራኘት

የወንጌል ስብከትንና ቤተክርስቲያንን የሚያገናኝ ትልቅ ምስል አለ። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የመጀመሪያ ምዕራፎች ያስተዋለን ከሆነ፣ ሐዋሪያቱ ትንሣኤውን ሲሰብኩ ከጀርባ ደግሞ በጋራ የሚኖሩ፣ ያላቸውን በአንድነት ያደረጉና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በሰዎች መሃከል በሞገስ የሚመላለሱ ሰዎች ያሉባት ቤተክርስቲያን ነበረች (2፥47፤ 5፥13)። በሆነ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ከወንጌል ስብከት ጀርባ እንደ ምስክር ሆኖ ያገለግላል። በኢየሩሳሌም የነበሩ ሰዎች ቅዱሳንን በሞገስ እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል፤ ብዙዎችንም ወደ ድነት የመራ ይመስላል።

Continue Readingወንጌል ስብከትን ከቤተ ክርስቲያን ጋር ማቆራኘት
ወንጌል መስበክ ምን ማለት ነው?

ወንጌል መስበክ ማለት ክርስቶስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ያደረገውን መልካም ዜና መናገር ነው። ይህንም ለማድረግ እነዚህን እውነቶች የግድ መናገር ይኖርብናል፦ 1. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው (1 ዮሐንስ 1፥5)። እርሱ የሚታይውም የማይታየውም ዓለም ፈጣሪ…

Continue Readingወንጌል መስበክ ምን ማለት ነው?
ወንጌል ምንድን ነው?

ወንጌል ምንድን ነው? በወንጌላውያን አማንያን ዘንድ ለረጅም ጊዜ እየተካሄዱ ካሉ ክርክሮች መካከል ዋነኛው “ወንጌልን በምን መልኩ እንረዳው?” የሚል ነው። የወንጌል ትርጉሙስ ምንድን ነው? አንዳንዶች እንደሚረዱት፣ “ወንጌል ማለት ኅጢአተኛ የሆኑ ሰዎች…

Continue Readingወንጌል ምንድን ነው?