ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥነ መለኮት ያለኝን ግንዛቤ እንዴት ማሳደግ እችላለሁ?

መልስ

  1. ጭብጦችንና ርዕሰ ጉዳዮችን በመያዝ መጽሐፍ ቅዱስን አጥኑ፦ ሁሉንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በስፋት እና በጥልቀት ማጥናት ቢገባም፣ በአጠቃላይ መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ጭብጦችን ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ግን እጅግ ጠቃሚ ነው። ፍጥረት እና አዲስ ፍጥረት፣ የሰንበት ዕረፍት፣ ንጉሣዊ አገዛዝ፣ ቃል ኪዳን እና በሕዝቡ መካከል የእግዚአብሔር ማደሪያ የመሳሰሉት ጭብጦችን በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት እያደጉ እንደ መጡ ካጠናችሁ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብር እና ስለ አስደናቂ ማዳኑ የተሻለ እይታ ይኖራችኋል።
  2. ብሉይ ኪዳንን ለማጥናት፣ አዲስ ኪዳናዊ አመለካከትን ያዙ አዲስ ኪዳንን በምታጠኑበት ጊዜ፣ እንዴት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት ሐሳቦች እንደተፈጸሙ፣ ይበልጥ ግልጽ እንደሆኑ እና ጎልተው እንደታዩ፣ አንዳንዴም እንዴት እንደተተኩ አስተውሉ። ይህንን ስታደርጉ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት አንድነትን፣ በታሪክ ውስጥ እግዚአብሔር ለማዳን ያለውን ወጥ ዓላማ እንዲሁም በተለያየ መንገድ የተገለጠውን የክርስቶስ የማዳን ሥራ ባለጠግነት ታስተውላላችሁ።
  3. ክርስቶስን እና አዲስ ኪዳንን በሚጠቁም መልኩ ብሉይ ኪዳንን አጥኑ፦ ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ፣ እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቁ፦ “ይህ ምንባብ፣ በድነት ታሪክ ውስጥ የቱ ጋር ይገኛል? ወደ ክርስቶስስ እንዴት ይጠቁማል? እንዴትስ ለክርስትና መሠረት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? የትኞቹ የአዲስ ኪዳን ምንባባትስ ይህንን ክፍል ይበልጥ እንድንረዳው ያግዙናል?”
  4. በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉትን የትንቢት መጻፍትን አጥኑ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኙት የትንቢት መጻሕፍት፣ የክርስቶስ ሕይወትና አገልግሎት እንዲሁም የእርሱን ልዕልና በሚያሳዩ ምንባባት የተሞሉ ናቸው። ስለ እግዚአብሔር ያለንን ዕውቀት ያሳድጋሉ፤ እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር የማዳን ሥራ ፍጻሜ ይጠቁማሉ።
  5. በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የሥነ መለኮት ላይ ጥሩ መጽሐፍ አንብቡ፦ በGraeme Goldsworthy በተጻፈው “The Goldsworthy Trilogy” ወይም የVaughan Roberts መጽሐፍ በሆነው “God’s Big Picture: Tracing the Storyline of the Bible” መጀመር ትችላላችሁ።