ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንለውጥ?

መጋቢዎች ብዙ ጊዜ እንዲህ ብለው ይጠይቁኛል፦ “አብያተ ክርስቲያኖቻችንን መለወጥ የምንችለው እንዴት ነው?” በጣም ብዙ አገልጋዮች ለውጥ ለማምጣት እየሞከሩ ቤተ ክርስቲያናቸውን አግልለዋል። አንዳንዶቹ ከኀላፊነት ተባረዋል። አሁንም እረኛ እንደ መሆናችን መጠን እንዲህ ያለው ለውጥ ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ለውጥ መምራት አለብን። ለውጥን እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ጥቂት ምክሮች ልበል፦ ለውጥን ማስተማር፣ መጠበቅ እና መውደድ ናቸው።

ስለ ለውጥ ማስተማር

በመጀመሪያ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ያለን ቅንዓት ከቅዱሳት መጻሕፍት ሊመነጭ ይገባል። ይህም ቤተ ክርስቲያንን ለመለወጥ መድረኮቻችን በጣም ኀይለኛ መሣሪያዎች ናቸው። ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በገላጭ ስብከት መስበክ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በመደበኛነት በሰው ልብ ውስጥ የሚሠራበት መንገድ ነው።

በስብከታችሁ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችሁን እንዴት መለወጥ እንዳለበት እንዲያስተምር ጸልዩ። የሚገርመው ነገር እኛ መጋቢዎች ችግሮቹን ለማብራራት ጊዜ ከመስጠታችን በፊት፣ ችግሮችን ለማስተካከል መፈለጋችን ነው!

በጣም ብዙ መጋቢዎች በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ ለውጥን አስገድደው ለማምጣት ይሞክራሉ፤ ለቤተ ክርስቲያን ለማሳወቅ ሲሞክሩ ብዙ ጊዜ እንደ አመራር ይሟገታሉ። ወንድሞች! በአደራ የተሰጡንን መንጎች ልንመግባቸው እንጂ ልንደበድባቸው አይገባም፤ አስተምሯቸው።

ያሰቡት ለውጥ ትክክል ቢሆንም፣ ጊዜው ትክክል ነው ወይ የሚለው ጥያቄ አሁንም አለ። ትክክል መሆን ለፈጣን እርምጃ ፈቃድ አይደለም፤ ይህም ወደ ሁለተኛው ነጥቤ ያደርሰኛል።

ለውጥን መጠበቅ

ለአንድ ቦታ መሰጠት የሚባለው ሐሳብ በሥራ ቦታ እና በቤት ውስጥ እየጠፋ ነው። ለሚመጣው ወጣት ትውልድ ለሞዴልነት የሚሆን መሰላል አይደለም። እያንዳንዳችን ሌላውን እንደምናንጽ በመረዳት ለተለያዩ ልምዶች ዋጋ እንድንሰጥ እየተማርን ነው።

እኛ መጋቢዎች በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተለየ አርአያ ማኖር አለብን። ለትዳራችን እና ለቤተ ሰቦቻችን፣ ለጓደኞቻችን እና ለእምነታችን፣ ወይም ለቤተ ክርስቲያናችን እና በአካባቢያችን ላሉ ቁርጠኝነት ጥሩ እንደሆነ ልናስተምራቸው ይገባናል። አብያተ ክርስቲያኖቻችን በትክክል ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች እንዲያገኙ መርዳት የምንችለው ከእንዲህ ዐይነቱ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነት አንፃር ነው (ከወራት ሳይሆን ከዐሥርት ዓመታት አንፃር)።

እንደ መጋቢ፣ የጉባኤያችሁን ለውጥ የመርዳት ታላቅ ኀይል የሚገኘው በጠንካራ ስብዕናችሁ ሳይሆን፣ ለብዙ ዓመታት በታማኝነት እና በትዕግሥት በማስተማር ነው። በዚህ ዓመት የማይከሰቱ ለውጦች በሚቀጥለው ዓመት ወይም በዐሥርት ዓመታት ውስጥ ሊመጡ ይችላሉ።

ለዚያም አንድን አስፈላጊ ለውጥ ከሌላው በማስቀደም ውጊያውን በጥበብና በጥንቃቄ ማካሄድ ያስፈልጋል። ከሚያስፈልጉት ለውጦች ውስጥ አሁን በጣም የሚያስፈልገው የትኛው ነው? የትኛውን መጠበቅ ይሻላል? በአጠቃላይ፣ ፓስተሮች በበሳል እይታ እንዴት ረዥም ርቀት መጓዝ እንደሚችሉ መማር አለባቸው።

ለረዥም ጊዜ የሚሆን መጋቢነት ራሱ መጋቢውን ይረዳሉ። የተንኮል ከረጢት ይዞ እንዳይመጣ፣ ነገሩን ለሁለትና ለሦስት ዓመታት እንዳያደርግ፣ ከዚያም እንዲቀጥል ያደርጉታል። በአጠቃላይ፣ በቆየን ቁጥር፣ የበለጠ ግልፅ መሆን አለብን፤ ደግሞም ይህ ለነፍሳችን እና ለምናገለግላቸው ሰዎች ጥሩ ነው።

ምዕመናንን ለማስተማር በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ረጅም ጊዜ መቆየት የለውጥ ቁልፍ ነው። ለመቆየት ካላሰቡ፣ የሚቀጥለው ሰው መጨረስ ያለበትን ነገር ከመጀመርዎ በፊት ይጠንቀቁ። በአንተ ወይም በሚተካህ ላይ ጉባኤው እንዲደነድን አትተወው።

ወጣት ተማሪ ሳለሁ ሦስት የካምብሪጅ አንግሊካን ቄሶችን እንደ ሞዴል አድርጌ ወሰድኩ። ሁሉም ለብዙ ዓመታት ቁልፍ ቦታዎች ላይ አገልጋዮች ነበሯቸው፦ ሪቻርድ ሲብስ (በካምብሪጅ እና ለንደን ለ30 ዓመታት)፣ ቻርለስ ሲሞን (በካምብሪጅ ከ50 ዓመታት በላይ የቆዩት) እና ጆን ስቶት (ለንደን ከ50 ዓመታት በላይ)ያገለገሉ ናቸው። በእግዚአብሔር ቸርነት፣ እነዚህ ሦስቱም ሰዎች የሚያገለግሉትን ቤተ ክርስቲያን ገነቡ፤ እናም በማደግ ላይ ያሉትን አገልጋይ ትውልዶች በረጅም ጊዜ በቆየ ታማኝነታቸው በማብቃት ፈጸሙ።

ለውጥን መውደድ

ትክክለኛ ለውጦችን ለመፈለግ፣ ስለ እነርሱ ለማስተማር እና ለረጅም ጊዜ ለመቆየት፣ ለውጥን መውደድ አለብን። ጌታን መውደድ አለብህ፣ አደራ የሰጣችሁንም ሕዝብ እንዲሁ።

የሮሜው ክሌመንት፣ “ክርስቶስ የእነርሱ የሚሆነው ልባቸው ትሑት ለሆኑት እንጂ፣ በመንጋው ላይ ራሳቸውን ከፍ ለሚያደርጉ አይደለም” ብሏል። ከፍቅር የሚመጣው ታጋሽ እንክብካቤ፣ ጉባኤውን ደጋግሞ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንዲዞር ያደርጋል።

ጆናታን ኤድዋርድስ ታማኝ መጋቢ ከመሆን ዝቅ አላለም፤ ምክንያቱም ጉባኤው ስላሰናበተው። አንዳንዶቻችን አጭር ጊዜ የቆዩ እና ታማኝ እረኞች ነበሩን። ግን እነዚህ የእኔ ሥጋት አይደሉም። በዚህ አጭር ጽሑፍ ለማንሣት የሞከርኩት በማስተማር፣ በመቆየት እና በመውደድ ጉባኤያችሁን እንዴት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ለውጥ እንደምትመሩ አንዳንድ ሐሳቦችን በአእምሮአችሁ ውስጥ ለማንሣት ነው።

ማርክ ዴቨር