መልስ
- የቤተ ክርስቲያን የዲሲፕሊን ሥርዐት የአንድን ሰው ኀጢአት ፊት ለፊት የመቃወም እና ወደ ንሰሓም የመምራት ተግባር ነው። ይህም ሰው የማይመለስ ከሆነ፣ ከባድ በሆነ ንሰሓ-አልባ ኀጢአት ምክንያት፣ አንድን ክርስቲያን ነኝ የሚልን ሰው፣ ከቤተ ክርስትያን አባልነት እና የጌታ እራትን ከመውሰድ ወደ ማገድ ደረጃም ሊደርስ ይችላል።
- ሰፋ አድርገን ስንመለከተው ዲሲፕሊን፣ ቤተ ክርስቲያን አባላቷ ቅድስናን እንዲከታተሉ እና ኀጢአትን እንዲቃወሙ ለማገዝ የምታደርገው ማንኛውም ዓይነት ተግባር ነው። ይህም ስብከትን፣ ትምህርትን፣ ጸሎትን፣ የኅብረት ዝማሬን፣ ተጠያቂነት የሞላበት ግንኙነትን፣ እንዲሁም የእረኞችንና የሽማግሌዎችን ፈሪሀ እግዚአብሔር የሞላበትን ክትትል ያጠቃልላል።
- አንዳንድ ጊዜ ሰዎች፣ የመጀመሪያውን “የማቅናት ዲሲፕሊን”፣ ሁለተኛውን ደግሞ “ገንቢ ዲሲፕሊን” ብለው በመጥራት፣ በእነዚህ ሁለት ዓይነት የዲሲፕሊን አደራረጎች መካከል ልዩነትን ይፈጥራሉ።
- የማቅናት ዲሲፕሊን፦ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ልክ እንደ ማቴዎስ 18፥15-17፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 5፥1-13፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 2፥6፣ እና 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥6-15 ባሉ ክፍሎች ላይ ተጠቅሷል፤ ደግሞም እንዲፈጸም ታዝዟል።
- ገንቢ ዲሲፕሊን፦ በአዲስ ኪዳን ልክ እንደ ኤፌሶን 4፥11-12 እና ፊልጵስዩስ 2፥1-18 ባሉ ክፍሎች ላይ፣ ቅድስናን ስለ መከታተል እና በእምነት እርስ በርስ ስለ መገንባት በሚገልጹ ብዙ ክፍሎች ውስጥ ገንቢ ዲሲፕሊን ተጠቅሷል። በእርግጥ፣ ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን የጻፏቸው የአዲስ ኪዳን መልእክቶች፣ ባመኑበት እምነት እንዲገነቡ እና እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለማገዝ ስለሆነ፣ ገንቢ ዲሲፕሊንን የማሳያ ምሳሌዎች አድርገን ልንወስዳቸው እንችላለን።