ወንጌል የሚፈታው መሠረታዊው ችግር ምንድን ነው?

መልስ

ወንጌል በዋነኝነት ፍላጎቶቻችንን ስለሟሟላት ነውን? ትርጉም የማግኘት ፍላጎታችንን ስለሟሟላት ነውን? ማኅበረሰቡን ስለመለወጥ ነውን? የተሻለ ሕይወት እንዴት እንደምንኖር ማስተማር ነው? ድኾችን ስለማንሣት ነውን? እኛን ሀብታም እና ጤናማ ስለማድረግ ነውን?

ስለ ወንጌል የሚታሰቡ እነዚህ ሁሉ ሐሳቦች በተመለከትናቸው ችግሮች ላይ ይጣበቁና “ወንጌሉ ስለዚህ ነገር ብቻ ነው!” ይላሉ። ነገር ግን ወንጌሉ ስለ እነዚህ ነገሮች ብቻ ነው? እነዚህ ነገሮች ወንጌሉ በመሠረታዊነት የሚመልሳቸው ችግሮች ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ “በፍጹም! የትኛቸውም አይደሉም” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር መሠረታዊ ችግር ኀጢአታችን ደግሞም በኀጢአታችን ምክንያት በእኛ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ቁጣ እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል።

  • “ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል?” (ናሆም 1፥6)
  • “በክፋታቸው እውነትን ዐፍነው በሚይዙ፣ በዐመፃቸውና በክፋታቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣል” (ሮሜ 1፥18)።
  • “ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ የሚመጣው በእንደዚህ ዐይነት ነገር ነው” (ኤፌሶን 5፥6)።
  • “ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዦች፣ የጦር መኰንኖች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ፤ ተራሮቹንና ዐለቶቹንም፣ “በላያችን ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቍጣቸው ቀን መጥቷልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሏቸው” (ራዕይ 6፥15–17)።

ወንጌል የሚመልሰው መሠረታዊ ችግር በኀጢአታችን ላይ ያለውን የእግዚአብሔር ቁጣ ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ማስተሰረያ ሆኖ ሞቶልናል፤ በእርሱ በማመን መዳን እንችል ዘንድ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚመልስ መሥዋዕት ነው (ሮሜ 3፥251ኛ ዮሐንስ 2፥24፥10)።