መጋቢ ሆይ! ስለ ቅድስና ያለህን ሥነ መለኮት ማወቅ አለብህ

በክርስትና ሕይወት ውስጥ ስላለው ቀጣይነት ያለው ቅድስና ያለኝን ጎዶሎ የሆነ ዕውቀት የተገነዘብኩበት ጊዜ እስካሁን ድረስ አዕምሮዬ ውስጥ ታትሞ ቀርቷል። ይህ አጋጣሚ በአንድ አነስተኛ ቡድን ውስጥ በእኛ የመቀደስ ሂደት ውስጥ የእኛ ድርጊት ድርሻና የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በምንወያይበት ወቅት ነው። ውይይታችን እየተደረገ በነበረበት ጊዜ ሰዎች በቅድስና እንዲያድጉ ምን እንደረዳቸው፣ ብሎም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅድስና ለማደግ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደተማሩ እያካፈሉ ነበር፤ ልክ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ፣ ጸሎት ወዘተ የመሳሰሉትን ነገሮች። ከዚህ በተጓዳኝ፣ ሰዎቹ በተደጋጋሚ መንፈስ ቅዱስ እነርሱን የመቀደስ ሥራውን እንደሠራ እየጠቀሱ ነበር። በስተመጨረሻ ግን አንዲት እውነተኛና ግልጽ የሆነች ሴት እንደመባረቅ ዐይነት ብላ “እኔ አይገባኝም፤ እንዴት ነው በክርስትና ማደግ የሚቻለው?” ብላ የሆዷን አፈነዳችው።

ትንሽ የጀርባ ታሪኩን ለመስጠት ይህች ሴት ለብዙ ዐመታት ኢየሱስን ተከትላለች፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እድገቷ እንደቆመ ይሰማታል። መጽሐፍ ቅዱስን ታነባለች፤ ትጸልያለች፤ እንዲሁም በየእሁዱ ቤተ ክርስቲያን አትቀርም። ሆኖም ግን በውስጧ በሰዎች ላይ ቂምና መራርነት ይዛለች፤ እንዲሁም የምትጸጸትባቸውን ነገሮች ሰዎችን ተናግራለች። ኅጢታቷም እግዚአብሔርን እንዳሳዘነ ተረድታለች። ስለዚህም ተረጋግታ እግዚአብሔር እስኪቀድሳት መጠበቅ እንደማትችል ታውቀዋለች። በዚህ ላይ ደግሞ አሁን እየገባት ያለው ነገር እርሷ እያሳየቸው ባለው ጥረት መጠን እድገቷ የዚያን ልክ ያለመሆኑን እውነታ ነው። በብዙ እየጣረች ነገር ግን የትም እየደረሰች አይደለም። በዚያው ማታ ቀደም ብሎ መንፈሳዊ ልምምዶቻችን ቀጥተኛ የዕድገታችን ምክንያቶች ካደረግናቸው እድገታችን አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ሐሳብ ሰጥቼ ነበር፤ ምክንያቱም ትኩረታችን ከክርስቶስ ወንጌል ይልቅ እኛ ላይ ስለሚሆን። በትክክል መናገር ምችለው የሰጠሁት ሐሳብ ምንም ቢያስፈራትም ከእርሷ ሕይወት ጋር ቀጥታ ተዛማጅነት ነበረው።

ይህም ሆኖ ጥያቄዋን መመለስ አልቻልኩም ነበር፤ ምክንያቱም ስለ ድነት የነበረኝ አመለካከት ቁርጥራጭ ነበር። ሙሉና ተፈጥሮዊ የሆነ የድነት አረዳድ ስለ ሌለኝ የድነት ሂደት አካል የሆኑት በእግዚአብሔር ፊት መጽደቅና ቀጣይነት ያለው የክርስትና ቅድስና እርስ በርስ ይጋጩብኝ ነበር። ሰዎች የመለስኩ እንዲመስላቸው ብቻ የተወሰነ እርስ በእርሱ የማይጣጣም ነገር ቀባጠርኩና ለእረፍት እንዲወጡ አደረኩ። ሆኖም ግን የተፈጠረውን ግርታ ምንም ሊፈታው አልቻለም።  

የመጋቢ ኅላፊነት

ሚስቴ ከሕፃን ሴት ልጃችን ጋር የእናትና ልጅ ሥነ ልቦናን ሳታብራራ እንደምትረዳ ሁሉ አንድ ክርስቲያንም ቀጣይነት ስላለው የክርስትና ቅድስና እድገት ሥነ መለኮት የግድ ማብራራት አለበት ብዬ አላስብም። ክርስቶስን እየተመገብን በደንብ ማደግ እንችላለን ምንም እንኳ እንዴት ይህ ሂደት እንደተፈጸመ ማስረዳት ባንችልም። ከላይ ያለውን ምሳሌ ለመቀጠል፣ በእናትና ሴት ሕፃን ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት መካከል የሆነ ችግር ቢከሰትስ? በእርግጠኝነት መናገር የምችለው የሆነ ሰው ችግሩን የሚረዳና ሊያግዝ የሚችል ሰው ይኖራል።

ለዚህም ነው መጋቢያን የቅድስናን ሥነ መለኮት ማወቅ የሚጠበቅባቸው። “ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካሪ ሥራ አይድለምን?” ብላቹ ልታስቡ ትችላላቹ መልሱ ልክ ነው የሚል ነው። ሆኖም ግን መጋቢያን ማለትም በዋነኝነት በማስተማርና በስብከት የሚያገለግሉ ሕዝቦቻቸውን በትክክለኛው አቅጣጫ ለመምራት ቀጣይነት ያለውን የክርስትና ቅድስና ሥነ መለኮት የማስተማት ሃላፊነት አለባቸው። አስቡት እስኪ ለሕዝባችሁ ቅድስናን ታሳቢ በማድረግ ካልሰበካቹ ምን እያደረጋቹ ነው? በአዕምሮ ዕውቀት ብቻ ሕዝባችሁን ማሳደግ እንደማታሰቡ አስባለሁ ከዚያም ሲብስ ሰዎችን አዝናንቶ የመላክ ሐሳብ እንደማይኖራችሁ እሙን ነው። ሕዝባችሁ የሕይወት ለውጥ እንዲያመጡ ትፈልጋላችሁ። ነገር ግን ጥያቄው ይህ እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጣችኋል ወይ ነው? ይህ ካልሆነ ሕዝባችሁ በትክክለኛው አቅጣጫ እየሄዱ እንደሆነ እንዴት ማወቅ ትችላላችሁ?

ምንድን ነው በተደጋጋሚ የምንስተው ነገር?

ቀጣይነት ያለው የክርስትና ቅድስና ላይ የተጋረጡት አደጋዎች አንዱ ቅጥ ያጣ ነፃነት ሲሆን ሌላው ደግሞ አጉል ወግ አጥባቂነት ናቸው። አጉል ወግ አጥባቂነት ቅድስናን እኛ እንደምንሠራው ሥራ ያየዋል። ምናልባት የተወሰኑ ሥራዎችን ብሰራ ድነቴን ማግኘት እችላለሁ ይላል። ወይም ደግሞ እነዚህን ማደርገው በእግዚአብሔር ዘንድ የተሻለ ሞገስ ለማግኘት ነው የሚል ሐሳብ አለው። “እነዚህን ነገሮች ባቆምና እንዚህን ነገሮች ብጀምር ጥሩ እሆናለሁ” ብሎም ያስባል። ይህ አጉል ወግ አጥባቂነት ነው ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ሕብረት የሚመነጭ መታዘዝ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት እንዲኖረን ለመታዘዝ መጣር ስለሆነ ነው።

ሁለተኛው ስሕተት ቅጥ ያጣ ነፃነት ነው፤ ይሄንን ደግሞ የሚቀበሉት ሕግ ጠሎች ይባላሉ። ይህ የተሳሳተ ሐሳብ የሚነሳው በክርስቶስ የተደረገልን ነገሮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እኛ መሥራት ላለብን ሥራ ምንም ክፍተት አይተውም። የሕግ ጠሎች ከፍተኛ ውድቀት የራሳቸው የተሳሳተ ተዛምዶና ጥረት መና ሲቀር የሚደርሱበት የተሳሳተ ድምዳሜ ጭራሹኑ ምንም ጥረት አለማድረግ የሚል ይሆናል።

እስቲ አሁን ደግሞ ለቅድስና ግልጽ አቅጣጫ ካልተቀመጠ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል እንመልከት። ሰዎችን አጉል ወቅ አጥባቂነታቸውን ቅጥ ባጣ ነፃነት እንዲዋጉት፣ በተቃራኒው ደግሞ ቅጥ ያጣ ነፃነትን በሕግኝነት እንዲዋጉት እናበረታታለን። አስታውሳለሁ! የተወሰኑ የኮሌጅ ተማሪዎች ወንጌልን መስበክ እንዳቆም ሲነግሩኝ፤ ምክንያቱም ለቅድስና ያላቸውን ፍላጎት አደጋ ላይ እየጣልው እንደሆነ ስለሚያስቡ። አንዳንድ የማውቃቸው ሰዎች አሉ በግልጽ ቢያወሩት ኅጢአትን በመሥራታቸው የሚጽናኑ፤ ምክንያቱም ሕግኛ ወይም አጉል ወግ አጥባቂ አለመሆናቸውን ስለሚያረጋግጥላቸው። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ቅድስና አይደለም፤ እኛም ቢሆን ይህን ዐይነት አስተሳሰብ በፍጹም ማበረታታት የለብንም።

የውሸት ቅድስናን ማስተዋወቅ ከምታስቡት በላይ ቀላል ነው። ብዙ ሰባኪዎችን ሰምቻለሁ በሕዝባቸው ላይ ብዙ ማድረግ ያለባቸውን ነገር እየጫኑ ነገር ግን በምን ኅይል ያንን ማድረግ እንደሚችሉ ምንም የማይናገሩ። የጳውሎስ “ስለዚህ ጸጋ እንዲጨምር በኅጢአት ፀንተን እንቀጥል?” ለሚለው ጥያቄ አዎን የሚል መልስ የሚመልሱ የሚመስሉ፣ ብዙ ጸጋና የቅድስና ኑሮ ግንኙነት የሌላቸው ነገሮች የሚያስመስሉ ስብከቶችን ሰምቻለሁ። እነዚህ ስሕተቶች የሚስተካከሉት የሁሉንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማዕከል ክርስቶስን ባደረጉ ስብከቶች ነው። ነገር ግን ቀጣይነት ያለው የቅድስና ሕይወት ሥነ መለኮት ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም አንድ እርምጃ ወደ ፊት በመሄድ “ክርስቶስ ጋር ስንደርስ እንዴት ነው ክርስቶስን መልበስ ምንችለው ብሎም ደግሞ እንዴት ነው ስጋ ምኞቱን እንዲፈጽም አለማሰብ የምንችለው?” ሚለውን ጥያቄ ለመጠየቅ።

አሁን እያልኩ ያለሁት እያንዳንዱ ስብከቶች ረጃጅም የቅድስና ሕይወት አስተምህሮን ማካተት አለባቸው አይደለም። በስብከታችን መካከል ክርስቶስ ጋር ስንደርስ በአንድ አረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል። ምናልባት በዚህ ሐሳብ ለተረበሸ ወይም በራሱ የበቃ ለመሰለው ሰው የምትናገሩት ነገር ሁሉም ሰው የሚያውቀው ወይም ግልጽ ነገር ነው ብሎ ሊያስብ ይችላል። ዋናው ነገር “ክርስቶስን መልበስ” እና “በላይ ያለውን ነገር ማሰብ” ከቅድስናችን ጋር ተያይዞ ዋነኛ ትዕዛዞች ከሆኑ ምን ማለት እንደሆኑ ማወቅ አለብን፤ ከዚያም ሲያልፍ በስብከታችን ውስጥ ግልጽ መሆን አለብን።

በክርስቶስ ውስጥ ያለው የቅድስና ኑሮ

ትክክለኛ የሆነ የቅድስና ሥነ መለኮት ጸጋን ሳይሸፍን የቅድስና እድገትን አስፈላጊነት ላይ አፅእኖት መስጠት አለበት። በተቃራኒው በቅድስና እንድገትን አስፈላጊነት ሳይቀንስ ጸጋ ላይ አጽእኖት መስጠት አለበት።

ይህን እንዴት ማድረግ እንችላለን? እዚህ ጋር አነስ ያለች ነገር ልጣልላቹ። የዚህ ጽሁፍ ትክክለኛ ግብ ስለ ቅድስና እንድታጠኑ ማድረግ ነው። የመጀመሪያው እርምጃ ቅድስናን ከድነት ጋር አያይዞ ማሳየት ነው። “ቅድስና” እና “መዳንን” እንደ ሁለት የተለያዩ እርስ በእርስ እንደሚወዳደሩ ነገሮች ምውራት ማቆም ይኖርብናል (ኤፌሶን 2፥8-9)። “ በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም” የሚለውን ጥቅስ “ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን” (ኤፌሶን 2፥10)። ከሚለው ለይቶ መጥቀስ ልናቆም ያስፈልጋል። ድነት ቀጣይነት ያለውን ቅድስናን ያካትታል፤ ነገር ግን እንደቅድመ ሁኔታ ሳይሆን እንደ አንድ ክፍሉ ነው። አትኩሮት መስጠት ያለብን ነገር፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነፃ ጸጋና መልካም ሥራ መካከል ምንም ውጥረት የለም።

ለምንድን ነው የሌለው?

ይህ ጥያቄ ወደ ሁለተኛው ሰፊ ሐሳብ ይመራኛል። ይኽውም ድነት ማለት በክርስቶስ ውስጥ መሆን ማለት ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አብዛኛውን ጊዜ ድነትን ስናስብ ተጠቅልለው እንደተከመሩ ብዙ ስጦታዎች ነው። ስጦታዎቹን ስም ለመስጠት ያክል አንዱ ስጦታ “ይቅርታን ማግኘት” ሌላው “መንፈስ ቅዱስ” አንዱ ደግሞ “ቤዛዎት” ሊሆን ይችላል።

እውነታው ድነት ማለት እኛ ለድነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የሆነውን ክርስቶስን ለድነታችን መቀበል ነው።እኛ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ውስጥ ነን።” ምክንያቱም ሁሉም ስጦታ እርሱን በመቀበል የሚገኝ ስለሆነ በእርሱ በኩል ፍጹም የሆነ ቅንጅት አላቸው። የኅጢአት ይቅርታና የተቆጠረልንን ጽድቅ ቁጭ ብሎ ለማረፍ ሳይሆን ምንጠቀምበት ይልቁንም ወደ ክርስቶስ ተጠግተን ከእርሱ በሚገኝ እርዳታ የጽድቅን ሕይወት ለመኖር ነው። ደግሞም የጽድቅን ሕይወት ስንኖር በእግዚአብሔር ፊት መጽደቃችንን ችላ አንለውም እንዳውም በእግዚአብሔር ቅድስና በመመሰጥ በክርስቶስ ስላገኘነው የተቆጠረለንን ጽድቅ የጨመረ አድናቆት ይኖረናል ይህም በእግዚአብሔር ፊት የመቆም መብታችን ነው። የክርስትና ሕይወታችንን የሚያያይዘው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው ፤ ይኽው ክርስቶስን ለጽድቃችን ከሞት ያሥነሳው መንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ ጋር ሕብረት እንዲኖረን ያደርጋል (ሮሜ 4፥25)፤ በፍሬ ይሞላናል ከዚያም በተጨማሪ እኛን ወክሎ በእግዚአብሔር ፊት ይጸልይልናል።

በሌላ አገላለጽ በድነታችን በኩል ያለው የትኛውም እድገት ያለጥርጥር ወደ ክርስቶስ ማንነት እና ከእርሱ ጋር ወዳለን መንፈሳዊ ሕብረት ጠልቀን እንድንገባ ያደርገናል ይህም በእርሱ ያገኘነው በረከት ጋር ያገናኘናል። በክርስቶስ ሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች የኛ ናቸው። ድነታችን እንደ አንድ ጥቅል ስናየው አንዱን ጥቅም (በረከት) ከሌላው ማበላለጥ አንችልም። ሲቀጥልም ሕግኝነትን ቅጥ ባጣ ነፃነት ለመዋጋት አንሞክርም። ሕግኝነትንም ሆነ ቅጥ ያጣ ነፃነትን በክርስቶስ እንዋጋቸዋለን።

ሴትየዋ ስለጠየቀችው ጥያቄ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቅድስናን እንዳጠና ስላነሳሳኝ። ምንም ያክል ይህ እውነት ቢገባንም ሁሌም ያልተረዳነው ነገር አለ፤ ከዚያም በላይ ከቁጥር በላይ የሆነ በሕይወታችን ልንለማመዳቸው የተገቡ ነገሮችም አሉ። መሠረታዊው የቅድስና አቅጣጭ እንኳ ካለን እርሱም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆነ የምንመራቸውን ሰዎች ወደ ክርስቶስ ጠልቀው እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፤ ይህም ወደ ጽድቅ ሕይወት ዘልቀው ይገባሉ ማለት ነው።

በወንጌላውያን መካከል በእግዚአብሔር ፊት የመቆም ጽድቅን (መጽደቅን) እንድንረዳ ከፍተኛ ግፊት አለ፤ ይህ ጥሩ ሆኖ ሳለ በክርስትና ቀጣይነት ያለውን መቀደሳችንን ችላ በማለት ግን መሆን የለበትም።

ማይክ ክራይስት