ለምን ሲኦል የወንጌሉ ቁልፍ ክፍል ሆነ?

ስለ ሲኦል[1] ማሰብ ማንን ደስ ያሰኘዋል? እንዲያውም “ስለ ሲኦል ከማሰብ ይልቅ ስለ ሌላ ማንኛውም ነገር ማሰብ የተሻለ ነው” ብለን እንድናስብ ከሚያስገድዱን ርዕሶች አንዱና ዋነኛው አይደለምን? ለአንዳንዶች እንዲያውም የክርስትና አስተምህሮ የሆነው ትምህርተ ሲኦል እና የትምህርቱ አስፈሪነት (ማለትም ሲኦል ዘላለማዊ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሁሉ በሙሉ ማንነታቸውና በሙሉ ንቃታቸው በማያቋርጥ ስቃይ የሚሰቃዩበት ቦታ መሆኑ)፣ ስለ እርሱ ማሰብን ወደ መሸሽ ብቻ ሳይሆን ከናካቴው ሲኦል የሚባል ነገር የለም ብሎ ወደ መደምደም የክህደት ጫፍ አድርሷቸዋል።

0 Comments