የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ምንድን ነው?

መልስ

  1. መሠረታዊ ሐሳብ፦ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ
  • ሀ) 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥1-7 እና ቲቶ 1፥6-9 ላይ ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ፣
  • ለ) በጉባኤው ሽማግሌ መሆኑ የሚታወቅ፣
  • ሐ) ደግሞም ጉባኤውን፣ ቃሉን በማስተማር (1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥2)፣ ለበጎቹ በመጸለይ (ያዕቆብ 5፥14)፣ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳዮች በመከታተል (1ኛ ጴጥሮስ 5፥2)፣ የሚመራ ሰው ነው።
  • 2. መከታተል፦ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ መንጋውን መጠበቅ አለበት። ሁሉንም በጎች መምራት፣ የደከሙትን ማበርታት፣ ለጥቃት የተጋለጡትን መጠበቅ፣ ግትር የሆኑትን መገሰጽ፣ እንዲሁም አስቸጋሪ የሆኑትን መታገስ አለበት (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥24-25ሐዋርያት ሥራ 20፥281ኛ ተሰሎንቄ 5፥14)። የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ እንደሆነ ሰው አባላቱን ይጠብቃል (ዕብራዊያን 13፥17)።
  • 3. ከአንድ በላይ መሆን፦ በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ሁልጊዜም ከአንድ በላይ ሽማግሌዎች አሏቸው (ሐዋርያት ሥራ 14፥2320፥17ፊልጵስዩስ 1፥11 ጢሞቲዎስ 5፥17ያዕቆብ 5፥14)። የእረኞች አለቃ የሆነው ክርስቶስ፣ መንጎቹን የሚንከባበከበው፣ በጋራ ሆነው በጎቹን በሚያስተምሩ፣ በሚጠብቁ፣ በሚመሩ እና በሚወዱ፣ እውነተኛ ፈሪሀ እግዚአብሔር ባላቸው ሰዎች (ወንዶች) በኩል ነው። ይህም ማለት፣ ሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት፣ የመጋቢያቸውን መሪነት በመከተል፣ የሽምግልና ሥራን በመሥራት ላይ የሚገኙ ሰዎችን(ወንዶች) በመለየት መሾም ይኖርባቸዋል።