ወንጌል መስበክ ማለት ክርስቶስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ያደረገውን መልካም ዜና መናገር ነው። ይህንም ለማድረግ እነዚህን እውነቶች የግድ መናገር ይኖርብናል፦
1. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው (1 ዮሐንስ 1፥5)። እርሱ የሚታይውም የማይታየውም ዓለም ፈጣሪ ነው።
2. ሰው ሁሉ ኀጢአተኛ ነው፤ ከዚህ የተነሣ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ የጽድቅ ፍርድ ይገባዋል (ሮሜ 3፥10-19፤ ማርቆስ 9፥48፤ ራእይ 14፥11 )።
3. ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዚህ ምድር ያለ ኀጢአት ተመላለሰ፤ በእርሱ ለሚያምኑ፣ በእነርሱ ፈንታ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመስቀል ላይ ተቀበለ፤ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ከሙታን ተነሣ (ዮሐንስ 1፥1፤ 1 ጢሞቴዎስ 2፥5፤ ዕብራውያን 7፥26፤ ሮሜ 3፥21-26፤ 2 ቆሮንቶስ 5፥21፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20-22)።
4.ከዘላለም ቅጣት ለማምለጥና ከእግዚአብሔር ጋራ ለመኖር ብቸኛው መንገድ ንስሓ መግባትና በክርስቶስ አዳኝነት ማመን ነው (ማርቆስ 1፥15፤ የሐዋርያት ሥራ 20፥21)።
ወንጌል መስበክ ማለት እነዚህን ወሳኝ ነገሮች ማሳወቅ ነው።